Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 27:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “ ‘ይሁዳና እስራኤል እንኳ ከአንቺ ጋራ ተገበያይተዋል፤ የሚኒትን ስንዴ፣ ጣፋጭ ቂጣ፣ ማር፣ ዘይትና በለሳን በማምጣት በሸቀጥሽ ይለውጡ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ይሁዳና የእስራኤል ምድር ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ዕቃዎችሽን በሚኒት ስንዴ፥ ጣፋጭ ዳቦ፥ ማር፥ ዘይትና በለሳን ይለውጡ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የይሁዳና የእስራኤል ነጋዴዎች ለሸቀጥሽ ዋጋ የሚኒት አገር ስንዴ፥ ማሽላ፥ ማር፥ የወይራ ዘይትና ቅመማ ቅመም ይከፍሉሽ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤል ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ስን​ዴ​ንም ይሸ​ም​ቱ​ልሽ ነበር፤ ሰሊ​ሆ​ት​ንና በለ​ሶ​ንን፥ ዘይ​ት​ንና የተ​ወ​ደደ ማርን፥ ርጢ​ን​ንም ከአ​ንቺ ጋር አንድ ይሆኑ ዘንድ ሰጡሽ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ይሁዳና የእስራኤል ምድር ነጋዴዎችሽ ነበሩ፥ የሚኒትን ስንዴ ጣፋጭም እንጕቻ፥ ማር ዘይትም በለሳንም ስለ አንቺ ሸቀጥ ይነግዱ ነበር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 27:17
9 交叉引用  

ከዚህ በኋላ አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፤ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ፤ ምድሪቱ ከምታፈራው ምርጥ ነገሮች ጥቂት በለሳን፣ ጥቂት ማር፣ ሽቱ፣ ከርቤ፣ ተምርና አልሙን በየስልቻችሁ ይዛችሁ ለዚያ ሰው እጅ መንሻ ውሰዱለት።


ሰዎቼ ግንዱን ከሊባኖስ እስከ ባሕሩ ድረስ ጐትተው ያወርዳሉ፤ እኔም ግንዱ ሁሉ ታስሮ አንተ እስከ ወሰንኸው ስፍራ በባሕር ተንሳፍፎ እንዲደርስ አደርጋለሁ፤ እዚያም እኔ እፈታዋለሁ፤ አንተም ትወስደዋለህ፤ አንተም ለቤተ ሰቤ ቀለብ በመስጠት ፍላጎቴን ታሟላለህ።”


ዕንጨቱን ለሚቈርጡ አገልጋዮችህ ሃያ ሺሕ የቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ ዱቄት፣ ሃያ ሺሕ የቆሮስ መስፈሪያ ገብስ፣ ሃያ ሺሕ የባዶስ መስፈሪያ ወይን ጠጅና ሃያ ሺሕ የባዶስ መስፈሪያ ዘይት እሰጣለሁ።”


ከዚያም ለድንጋይ ጠራቢዎችና ለየእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ገንዘብ ሰጡ፤ ከፋርስ ንጉሥ ከቂሮስ በተፈቀደው መሠረት የዝግባ ዛፎች ከሊባኖስ ወደ ኢዮጴ በባሕር እንዲያመጡላቸው፣ ለሲዶናና ለጢሮስ ሰዎችም ምግብ፣ መጠጥና ዘይት ሰጡ።


በገለዓድ የሚቀባ መድኀኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም አልነበረምን? ለሕዝቤ ቍስል፣ ለምን ፈውስ አልተገኘም?


እርሱም ከጢሮስና ከሲዶና ሰዎች ጋራ ጥለኛ ነበር፤ አገራቸው ምግብ የሚያገኘው ከንጉሡ ግዛት ስለ ነበር፣ የንጉሡን ባለሟል የብላስጦስን ድጋፍ ካገኙ በኋላ፣ አንድ ላይ ሆነው ከንጉሡ ጋራ ለመታረቅ ጠየቁ።


የላሙንና የበጉን መንጋ ቅቤና ወተት፣ የሰቡትን በጎችና ፍየሎች፣ የባሳንን ምርጥ አውራ በግ፣ መልካም የሆነውንም ስንዴ፣ ማለፊያውንም የወይን ጠጅ።


ስንዴና ገብስ፣ ወይንና የበለስ ዛፎች፣ ሮማን፣ የወይራ ዘይትና ማር የሚገኝባት ምድር፤


ከአሮዔር አንሥቶ እስከ ሚኒት አካባ፣ ከዚያም ዐልፎ እስከ ክራሚም የሚገኙትን ሃያ ከተሞች ፈጽሞ አጠፋቸው፤ አሞናውያንም ለእስራኤል ተገዙ።


跟着我们:

广告


广告