Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 27:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “ ‘ምርትሽ ብዙ እንደ መሆኑ፣ ሶርያ ከአንቺ ጋራ ትገበያይ ነበር፤ ሸቀጥሽንም በበሉር፣ በሐምራዊ ጨርቅ፣ በወርቀ ዘቦ፣ በጥሩ በፍታ፣ በዛጐልና በቀይ ዕንቍ ይለውጡ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከምርትሽ ብዛት የተነሣ አራም ነጋዴሽ ነበረች፤ ዕቃዎችሽን በበሉር፥ በወይን ጠጅ፥ በወርቀ ዘቦ፥ በጥሩ በፍታም በዛጐልም በቀይ ዕንቁም ይቀይሩ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የሶርያ ሕዝብ የንግድ ሸቀጥሽን ሁሉና ሌሎችንም ብዙ ዕቃዎች ይገዙሽ ነበር፤ በወሰዱአቸውም ዕቃዎች ምትክ በሉር፥ ሐምራዊና በጥልፍ ያጌጠ ልብስ፥ ቀጭን ሐር፥ ከዛጎል የተሠሩ ጌጣጌጦችና ቀይ ዕንቊ ይሰጡሽ ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የሶ​ር​ያም ሰዎች ከገ​ን​ዘ​ብሽ ብዛት የተ​ነሣ ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፥ ከአ​ን​ቺም ጋር አንድ ከሆኑ ከብዙ ሰዎች ጋር ትነ​ግጂ ነበር፤ ነጭ ሐር​ንና ዕን​ቍን፥ ቀይ ሐር​ንና ወርቀ ዘቦን ከር​ከ​ዴን የሚ​ባል ዕን​ቍ​ንና ልባ​ን​ጃም የሚ​ባል ሽቱን ከተ​ር​ሴስ ያመ​ጡ​ልሽ ነበር፤ ገበ​ያ​ሽ​ንም ረዓ​ሙ​ትና ቆር​ኮር መሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ከሥራሽ ብዛት የተነሣ ሶርያ ነጋዴሽ ነበረች በበሉርና በቀይ ሐር በወርቀ ዘቦም በጥሩ በፍታም በዛጐልም በቀይ ዕንቁም ስለ አንቺ ሸቀጥ ይነግዱ ነበር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 27:16
12 交叉引用  

የሴም ልጆች፦ ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ናቸው።


ይሥሐቅም ያዕቆብን በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ወደሚኖረው፣ የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም ወደ ሆነው ወደ ሶርያዊው የባቱኤል ልጅ ወደ ላባ ላከው።


አሞናውያን፣ ዳዊት እንደ ጠላቸው ባወቁ ጊዜ፣ ከቤትሮዖብና ከሱባ ሃያ ሺሕ ሶርያውያን እግረኛ ወታደሮችን እንዲሁም የመዓካን ንጉሥ ከአንድ ሺሕ ሰዎቹ ጋራ ደግሞም ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺሕ ሰዎች ቀጠሩ።


እኔ አገልጋይህ በሶርያ ምድር በጌሹር ሳለሁ ‘እግዚአብሔር ወደ ኢየሩሳሌም የመለሰኝ እንደ ሆነ፣ በኬብሮን ለእግዚአብሔር እሰግዳለሁ’ ብዬ ተስያለሁ።”


ሶርያውያንም የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ለመርዳት ከደማስቆ በመጡ ጊዜ ዳዊት ሃያ ሁለት ሺሕ ሰው ገደለ።


ወርቀ ዘቦ አለበስሁሽ፤ ምርጥ ቈዳ ጫማም አደረግሁልሽ፤ ያማረ በፍታ አለበስሁሽ ውድ መደረቢያም አጐናጸፍሁሽ።


በወርቅና በብር አጌጥሽ፤ ልብስሽም ያማረ በፍታ፣ ሐርና ወርቀ ዘቦ ነበር፤ ምግብሽም የላመ ዱቄት፣ ማርና የወይራ ዘይት ነበር። እጅግ ውብ ሆንሽ፤ ንግሥት ለመሆንም በቃሽ።


ወርቀ ዘቦ ልብስሽን ወስደሽ ደረብሽላቸው፤ ዘይቴንና ዕጣኔንም በፊታቸው አቀረብሽ።


ይህም ኀጢአትሽ ከመገለጡ በፊት ነበር። አሁን ግን በዙሪያሽ ሆነው ለሚንቁሽ ለኤዶም ሴት ልጆችና ለጎረቤቶቿ ሁሉ፣ እንዲሁም ለፍልስጥኤም ሴት ልጆች መሣለቂያ ሆነሻል።


በእግዚአብሔርም የአትክልት ቦታ፣ በዔድን ነበርህ፤ እያንዳንዱ የከበረ ድንጋይ አስጊጦህ ነበር፤ ሰርድዮን፣ ቶጳዝዮን፣ አልማዝ፣ መረግድ፣ ኢያሰጲድ፣ ሰንፔር፣ በሉር፣ ቢረሌና የከበረ ዕንቍ። ልብስህም የሚያብረቀርቅ ዕንቍ ወርቅ ነበር፤ የተዘጋጁትም አንተ በተፈጠርህበት ዕለት ነበር።


እስራኤላውያን እንደ ገና በእግዚአብሔር ላይ ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ በኣልንና አስታሮትን እንዲሁም የአራምን፣ የሲዶናን፣ የሞዓብን፣ የአሞንንና የፍልስጥኤማውያንን አማልክት አመለኩ፤ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ስለ ተዉና ስላላገለገሉት፣


跟着我们:

广告


广告