Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 26:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እርሱ መኻል አገር ያሉ ሰፈሮችሽን በሰይፍ ያወድማቸዋል፤ በዙሪያሽ ካብ ይክባል፤ እስከ ቅጥሮችሽ ጫፍ ድረስ ዐፈር ይደለድልብሻል፤ ጋሻውንም በአንቺ ላይ ያነሣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በሜዳ ያሉትን ሴቶችን ልጆችሽን በሰይፍ ይገድላቸዋል፤ በአንቺ ላይ ምሽግ ይሠራል፥ ደለልም በአንቺ ላይ ይደለድላል፥ በአንቺም ላይ ጋሻ ያነሣል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በዋናይቱ ምድር ባሉት መንደሮች ነዋሪ የሆኑ ሕዝብ ሁሉ በጦርነት ያልቃሉ፤ እናንተን የሚከላከልበት ምሽግ ይሠራል። ጠላትም እስከ ቅጽሮችሽ ጫፍ ዐፈር ይደለድላል፤ በጋሻም ብዛት እየተከላከለ ያጠቃችኋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እርሱ በም​ድረ በዳ ያሉ ሴቶች ልጆ​ች​ሽን በሰ​ይፍ ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል፤ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ንም በአ​ንቺ ላይ ያስ​ቀ​ም​ጣል፤ በዙ​ሪ​ያ​ሽም ግንብ ይሠ​ራል፤ የጦር መሣ​ሪ​ያም ይዘው ይከ​ቡ​ሻል፤ በጦ​ራ​ቸ​ውም ይወ​ጉ​ሻል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በሜዳ ያሉትን ሴቶችን ልጆችሽን በሰይፍ ይገድላቸዋል፥ አምባም ይሠራብሻል አፈርንም ይደለድልብሻል ጋሻም ያነሣብሻል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 26:8
9 交叉引用  

ከኢዮአብ ጋራ ያለውም ሰራዊት መጥቶ፣ ሳቤዔን በአቤል ቤትመዓካ በኩል ከበበው፤ በስተ ውጭም እስከ ከተማዪቱ ግንብ ጫፍ ድረስ ዙሪያውን የዐፈር ድልድል ሠሩ፤ ግንቡን ለመናድ በኀይል በሚደበድቡበት ጊዜ፣


“እነሆ፤ ከተማዪቱን ለመያዝ የዐፈር ድልድል በዙሪያዋ ተሠርቷል፤ ከሰይፍ፣ ከራብና ከቸነፈር የተነሣ ከተማዪቱን ለሚወጓት ለባቢሎናውያን ዐልፋ ልትሰጥ ነው፤ እንደምታየውም የተናገርኸው እየተፈጸመ ነው።


ስለዚህ ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሰራዊቱን ሁሉ አስከትቶ በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ፤ ከተማዪቱንም ከበቧት፤ በዙሪያውም የዐፈር ድልድል ሠሩ።


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “ዛፎቹን ቍረጡ፤ በኢየሩሳሌም ዙሪያ የዐፈር ድልድል ሥሩ። ይህች ከተማ ቅጣት ይገባታል፤ ግፍን ተሞልታለችና።


የቅጥር መደርመሻ አምጥቶ እንዲያቆም፣ ለመግደል ትእዛዝ እንዲሰጥ፣ ፉከራ እንዲያሰማ፣ ቅጥር መደርመሻውን በከተሞች በር ላይ እንዲያደርግ፣ የዐፈር ድልድል እንዲያበጅና ምሽግ እንዲሠራ የኢየሩሳሌም ዕጣ በቀኝ እጁ ወጣ።


መኻል አገር ያሉ ሰፈሮቿም በሰይፍ ይወድማሉ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’


ግንብ መደርመሻውን በቅጥሮቿ ላይ ያነጣጥራል፤ በመሣሪያም ምሽጎችሽን ያፈርሳል።


ነገሥታትን ይንቃል፤ በገዦችም ላይ ያፌዛል፤ በምሽግ ሁሉ ላይ ይሥቃል፤ የዐፈር ቍልል ሠርቶም ይይዘዋል።


ጠላቶችሽ ዙሪያሽን ቅጥር ሠርተው፣ ከየአቅጣጫውም ከብበው አንቺን የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣልና፤


跟着我们:

广告


广告