Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 26:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከፈረሶቹ ብዛት የተነሣ ዐቧራ ይሸፍንሻል፤ ሰዎች ቅጥሮቿ ወደ ፈረሱ ከተማ እንደሚገቡ እርሱ በበሮችሽ በሚገባበት ጊዜ፣ ከፈረሶቹና ከጋሪዎቹ፣ ከሠረገሎቹም ድምፅ የተነሣ ቅጥሮችሽ ይናወጣሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከፈረሶቹ ብዛት የተነሣ አቧራቸው ይሸፍንሻል፤ ሰዎች ወደ ፈረስች ከተማ እንደሚገቡ እርሱ በበሮችሽ በሚገባበት ጊዜ፥ ከፈረሰኞች፥ ከመንኩራኩሮች እና ከሰረገሎች ድምፅ የተነሣ ቅጥሮችሽ ይናወጣሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በፈረሶቻቸው ኮቴ የሚነሣው አቧራ እንደ ደመና ሆኖ ይሸፍንሻል፤ እርሱ ወደ ቅጥር በሮችሽ በሚገባበት ጊዜ ከፈረሰኛው፥ ከሠረገላውና ከመንኰራኲሩ የሚሰማው ድምፅ ተጥሳ እንደሚገባባት ከተማ ቅጥሮችሽን ያናጋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ከፈ​ረ​ሶ​ቹም ብዛት የተ​ነሣ በት​ቢያ ይሸ​ፍ​ን​ሻል፤ ከሠ​ረ​ገላ መን​ኰ​ራ​ኵ​ርና ከፈ​ረ​ሶቹ ድምፅ የተ​ነ​ሣም ቅጥ​ሮ​ች​ሽን ያፈ​ር​ሳል፤ ወን​በዴ መሣ​ሪ​ያ​ውን ይዞ ወደ ምድረ በዳ ቦታ እን​ዲ​ገባ በሮ​ች​ሽን ይገ​ቡ​ባ​ቸ​ዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ከፈረሶቹም ብዛት የተነሣ ትቢያቸው ይከድንሻል፥ ሰዎችም በተናደች ቅጥር ወደ ከተማ እንደሚገቡ እርሱ በበሮችሽ ሲገባ፥ ከፈረሰኞችና ከመንኵራኵሮች ከሰረገሎችም ድምፅ የተነሣ ቅጥርሽ ትናወጣለች።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 26:10
11 交叉引用  

የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ፦ የሳምጋሩ ኤርጌል ሳራስር፣ ጠቅላይ አዛዡ ናቦሠርሰኪም፣ ከፍተኛው ሹም ኤርጌል ሳራሳር እንዲሁም ሌሎቹ የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ ገብተው በመካከለኛው በር ተቀመጡ።


እነሆ፤ እንደ ደመና ይንሰራፋል፤ ሠረገሎቹ እንደ ዐውሎ ነፋስ ይመጣሉ፤ ፈረሶቹም ከንስር ይፈጥናሉ፤ መጥፋታችን ነውና ወዮልን!


ከፈረስ ኮቴ ድምፅ፣ ከጠላት ሠረገላ ጩኸትና ከሠረገላው ሽክርክሪት ፍትጊያ ድምፅ የተነሣ፣ አባቶች ልጆቻቸውን ለመርዳት ወደ ኋላ መለስ አይሉም፤ እጃቸውም ስንኩል ይሆናል።


እነርሱም የጦር መሣሪያ፣ ሠረገላና ጋሪ በመያዝ ብዙ ሕዝብ ሆነው ይመጡብሻል፤ ትላልቅና መለስተኛ ጋሻ በማንገብና የራስ ቍር በመድፋት በየአቅጣጫው ይሰለፉብሻል፤ እኔም ለፍርድ በእጃቸው አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ በሕጋቸውም መሠረት ይቀጡሻል።


“ጌታ እግዚአብሔር ጢሮስን እንዲህ ይላል፤ ‘የቈሰሉት ሲያቃስቱ፣ በውስጥሽም ጭፍጨፋ ሲካሄድ፣ ከውድቀትሽ ድምፅ የተነሣ ደሴቶች አይነዋወጡምን?


“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘የነገሥታት ንጉሥ የሆነውን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ከፈረሶችና ከሠረገሎች ጋራ፣ ከፈረሰኞችና ከታላቅ ሰራዊትም ጋራ ከሰሜን በጢሮስ ላይ አመጣለሁ።


ግንብ መደርመሻውን በቅጥሮቿ ላይ ያነጣጥራል፤ በመሣሪያም ምሽጎችሽን ያፈርሳል።


መርከበኞችሽ ሲጮኹ፣ የባሕሩ ጠረፍ ይናወጣል።


መለከቱ ሲነፋ ሕዝቡ ጮኸ፤ የመለከቱ ድምፅ ተሰምቶ፣ ሕዝቡ በኀይል ሲጮኽ ቅጥሩ ፈረሰ፤ እያንዳንዱም ሰው ሰተት ብሎ ገባ፤ ከተማዪቱም በእጃቸው ወደቀች።


የማያቋርጥ የመለከት ድምፅ ሲነፋ በምትሰሙበት ጊዜ፣ ሕዝቡ ሁሉ ከፍ ያለ ጩኸት ያሰማ፤ ከዚያም የከተማዪቱ ቅጥር ይፈርሳል፤ ሕዝቡም ወደ ላይ ይወጣል፤ እያንዳንዱም ሰው በቀጥታ ይገባል።”


跟着我们:

广告


广告