Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 24:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ሕዝቅኤል ምልክት ይሆናችኋል፤ እርሱ እንዳደረገው ታደርጋላችሁ፤ ይህ በሚሆንበት ጊዜ፣ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እንግዲህ ሕዝቅኤል ምልክት ይሆናችኋል፤ እርሱ ያደረገውን ሁሉ እናንተም ታደርጋላችሁ። ይህ በሚመጣበት ጊዜ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 በዚህም ዐይነት ሕዝቅኤል ለእናንተ ምልክት ይሆናል፤ እርሱ እንዳደረገውም ታደርጋላችሁ፤’ ይህ በሚፈጸምበት ጊዜ እኔ ልዑል እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ሕዝ​ቅ​ኤ​ልም ምል​ክት ይሆ​ና​ች​ኋል፤ እርሱ እንደ አደ​ረገ ሁሉ እና​ንተ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ፤ ይህም በመጣ ጊዜ እኔ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ሕዝቅኤልም ምልክት ይሆናችኋል፥ እርሱ እንዳደረገ ሁሉ እናንተ ታደርጋላችሁ፥ ይህም በመጣ ጊዜ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 24:24
24 交叉引用  

ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ባሪያዬ ኢሳይያስ ሦስት ዓመት በግብጽና በኢትዮጵያ ለምልክትና ለማስጠንቀቂያ ዕርቃኑንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፣


እነሆ፤ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሰራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ለእስራኤል ምልክትና ድንቅ ነን።


እነርሱ ደጋግመው፣ “የእግዚአብሔር ቃል የት አለ? እስኪ አሁን ይፈጸም!” ይሉኛል።


‘እኔ ምልክታችሁ ነኝ’ በላቸው። “እኔ እንዳደረግሁት፤ እንዲሁ በእነርሱ ይደረግባቸዋል፤ በምርኮኛነትም ተሰድደው ይሄዳሉ።


በፊታቸው ጓዝህን በትከሻህ ላይ አስቀምጥ፣ በምሽትም ተሸክመህ ውጣ። ለእስራኤል ቤት ምልክት አድርጌሃለሁና ምድሪቱን እንዳታይ ፊትህን ሸፍን።”


የዱር ዛፎች ሁሉ ረዥሙን ዛፍ፣ ዝቅ ዝቅ ያለውንም ዛፍ ከፍ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ የለመለመውን ዛፍ አደርቃለሁ፤ ደረቁንም አለመልማለሁ። “ ‘እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ እኔው አደርገዋለሁ።’ ”


የእስራኤል ቤት ሆይ፤ እንደ ክፉ መንገዳችሁና እንደ ብልሹ ተግባራችሁ ሳይሆን፣ ስለ ስሜ ስል በምጐበኛችሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”


ሞዓብንም እቀጣለሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”


በሕዝቤ በእስራኤል አማካይነት ኤዶምን እበቀላለሁ፤ እነርሱም እንደ ቍጣዬና እንደ መዓቴ መጠን በኤዶም ሕዝብ ላይ ያደርጋሉ፤ ኤዶማውያንም በቀሌን ያውቃሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”


በታላቅ በቀል እበቀላቸዋለሁ፤ በመዓቴም እቀጣቸዋለሁ፤” በምበቀላቸውም ጊዜ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”


የረባት ከተማ የግመሎች መሰማሪያ፣ አሞንንም የበጎች መመሰጊያ አደርጋለሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።


ክንዴን በእናንተ ላይ አነሣለሁ፤ በአሕዛብ እንድትበዘበዙ አደርጋለሁ፤ ከሕዝቦች መካከል አውጥቼ፣ ከአገሮችም ለይቼ አጠፋችኋለሁ፤ እደመስሳችኋለሁም። በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።’ ”


የብረት ምጣድ ወስደህ በአንተና በከተማዪቱ መካከል እንደ ብረት ቅጥር አቁመው፤ ፊትህንም ወደ እርሷ አዙር፤ የተከበበች ትሆናለች፤ አንተም ትከብባታለህ። ይህም ለእስራኤል ቤት ምልክት ይሆናል።


የታረዱ ሰዎቻችሁ በመካከላችሁ ይወድቃሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።


ንጉሡ ያለቅሳል፤ መስፍኑ ተስፋ መቍረጥን ይከናነባል፤ የምድሪቱም ሕዝብ እጅ ትንቀጠቀጣለች። የእጃቸውን እከፍላቸዋለሁ፤ ራሳቸው ባወጡት መስፈርት መሠረት እፈርድባቸዋለሁ። “ ‘በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”


በርኅራኄ ዐይን አልመለከትሽም፤ ምሕረት አላደርግልሽም፤ ስለ አካሄድሽና በመካከልሽ ስላለው ጸያፍ ተግባር፣ ተገቢውን ቅጣት እከፍልሻለሁ፤ በዚያ ጊዜ፣ የምቀሥፍ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።


ይህም ለመመስከር ጥሩ ዕድል ይሆንላችኋል።


“ሲፈጸም እኔ እንደ ሆንሁ ታምኑ ዘንድ፣ ይህ ከመሆኑ በፊት አሁን ነገርኋችሁ።


የተናገርሁት ሲፈጸም እንድታምኑ፣ ከመሆኑ በፊት አሁን ነግሬአችኋለሁ።


አስቀድሜ ይህን የነገርኋችሁ ጊዜው ሲደርስ እንድታስታውሱ ነው፤ ከእናንተ ጋራ ስለ ነበርሁ፣ ይህን ከመጀመሪያው አልነገርኋችሁም።


跟着我们:

广告


广告