Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 23:34 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ትጠጪዋለሽ፤ ትጨልጪዋለሽም፤ ከዚያም ጽዋውን ትሰባብሪዋለሽ፤ ጡትሽንም ትቈራርጪአለሽ፤ እኔ ተናግሬአለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ትጠጪዋለሽ፥ ትጨልጪዋለሽም፥ ገሉን ታኝኪዋለሽ፥ ጡትሽንም ትቆራርጪአለሽ፤ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ምንም ሳታስቀሪ ጨልጠሽ ትጠጪዋለሽ፤ ጽዋውንም ሰባብረሽ በስባሪው በሐዘን ጡቶችሽን ትቈራርጪአለሽ። እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ትጠ​ጪ​ዋ​ለሽ፥ ትጨ​ል​ጪ​ው​ማ​ለሽ፤ በዓ​ላ​ት​ሽ​ንና መባ​ቻ​ዎ​ች​ሽን እሽ​ራ​ለሁ፤ እኔ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ትጠጪዋለሽ ትጨልጪውማለሽ ገሉንም ታኝኪዋለሽ ጡትሽንም ትሸነትሪዋለሽ፥ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 23:34
7 交叉引用  

በእግዚአብሔር እጅ ጽዋ አለ፤ በሚገባ የተቀመመና ዐረፋ የሚወጣው የወይን ጠጅ ሞልቶበታል፤ ይህን ከውስጡ ወደ ውጭ ገለበጠው፤ የምድር ዐመፀኞችም አተላውን ሳይቀር ይጨልጡታል።


እኔ ግን ይህን ለዘላለም ዐውጃለሁ፤ ለያዕቆብም አምላክ ዝማሬ አቀርባለሁ።


ከእግዚአብሔር እጅ፣ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ፣ ዝቃጩ እንኳ ሳይቀር፣ ሰዎችን የሚያንገደግደውን ዋንጫ የጨለጥሽ፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ተነሺ!


እኔ ልቀጣሽ በምነሣበት ጊዜ፣ በልበ ሙሉነት መቆም ትችያለሽን? ወይስ እጅሽ ሊበረታ ይችላልን? እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ አደርገዋለሁም።


ገና በወጣትነታቸው ዘማውያት በመሆን በግብጽ ሳሉ አመነዘሩ፤ በዚያችም ምድር አጐጠጐጤአቸው ተዳበሰ፤ የድንግልናቸውም ጕያ በእጅ ተሻሸ።


በግብጽ የጀመረችውን አመንዝራነቷን አልተወችም፤ በዚያ ወንዶች በወጣትነቷ ከርሷ ጋራ ተኙ፤ የድንግልናዋን ጡት አሻሹ፤ ፍትወታቸውን አፈሰሱባት።


ለራሷ ክብርና ምቾት የሰጠችውን ያህል፣ ሥቃይና ሐዘን ስጧት፤ በልቧም እንዲህ እያለች ትመካለች፤ ‘እንደ ንግሥት ተቀምጬአለሁ፤ መበለትም አይደለሁም፤ ከቶም አላዝንም፤’


跟着我们:

广告


广告