Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 23:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “በአመንዝራነቷ እየባሰች ሄደች፤ በደማቅ ቀይ ቀለም በግድግዳ ላይ የተቀረጹ የከለዳውያንን ወንዶች ምስል አየች፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አመንዝራነቷን ቀጠለችበት፤ በቀይ ቀለም የተሳለ የከለዳውያን ስዕል፥ በግድግዳ ላይ የተቀረጸ የወንዶች ምስል አየች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14-15 “አመንዝራነትዋም እየባሰ ሄደ፤ በወገቦቻቸው ዙሪያ የሚያማምሩ ቀለበቶችን ታጥቀው፥ በራሶቻቸውም ላይ ጌጠኛ ጥምጥም ጠምጥመው፥ በደማቅ ሐምራዊ ቀለም በግድግዳ ላይ የተቀረጹትን ከፍተኞች የሆኑት ባለሥልጣኖችን ምስሎች አይታ ተማረከች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ዳግ​መ​ኛም ዝሙ​ቷን አበ​ዛች፤ በግ​ንብ ላይ የተ​ሣሉ የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሰዎች ሥዕ​ል​ንም አየሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ግልሙትናዋንም አበዛች፥ በቀይ ቀለምም የተሳለችውን የከለዳውያንን ስዕል፥ በናስ ላይ የተሳሉትን ሰዎች አየች።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 23:14
9 交叉引用  

ቤል ተዋረደ፤ ናባው እጅግ ዝቅ አለ፤ ጣዖቶቻቸው በአጋሰስ ተጭነዋል፤ ይዘዋቸው የሚዞሩት ምስሎች ሸክም ናቸው፤ ለደከሙ እንስሳት ከባድ ጭነት ናቸው።


‘ባለትልልቅ ሰገነት፣ ሰፊ ቤተ መንግሥት ለራሴ እሠራለሁ’ ለሚል ወዮለት! ሰፋፊ መስኮቶችን ያበጅለታል፤ በዝግባ ዕንጨት ያስጌጠዋል፤ ቀይ ቀለምም ይቀባዋል።


“በሕዝቦች መካከል ተናገሩ፤ አስታውቁም፤ ሰንደቅ ዐላማ አንሡ፤ ዐውጁ፤ አንዳች ሳታስቀሩ፣ እንዲህ በሉ፤ ‘ባቢሎን ትያዛለች፤ ቤል ይዋረዳል፤ ሜሮዳክ በሽብር ይሞላል፤ ጣዖቶቿ ይዋረዳሉ፤ አማልክቷም ይሸበራሉ።’


ርኩሰትሽንም እስከ ነጋዴዎች ምድር እስከ ባቢሎን ድረስ አበዛሽ፤ ያም ሆኖ አልረካሽም።


ይህችም እንደ ረከሰች አየሁ፤ ሁለቱም በአንድ መንገድ ሄዱ።


እነርሱም ወገባቸውን በቀበቶ የታጠቁና በራሳቸው ላይ ተንጠልጣይ ያለው ጥምጥም የጠመጠሙ ነበሩ፤ ሁሉም የከለዳውያን ተወላጆችና የባቢሎን ሠረገላ አዛዦች ይመስሉ ነበር።


እነርሱም ባቢሎናውያንና ከለዳውያን ሁሉ፣ የፋቁድ፣ የሱሔና የቆዓ ሰዎች፣ ከእነርሱም ጋራ አሦራውያን ሁሉ ናቸው። እነዚህም መልከ ቀና ጐበዛዝት ሲሆኑ፣ ሁላቸውም በፈረስ ላይ የተቀመጡ ገዦችና አዛዦች፣ የሠረገላ አዛዦችና ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ነበሩ።


እኔም ገብቼ አየሁ፤ እነሆ የሚሳቡ ፍጥረታትና የርኩሳን አራዊት ዐይነት ሁሉ፣ የእስራኤልም ቤት ጣዖታት ሁሉ ዙሪያውን በግንቡ ላይ ተቀርጸው ነበር።


የወታደሮቹ ጋሻ ቀይ ነው፤ ተዋጊዎቹ ቀይ ልብስ ለብሰዋል፤ ዝግጁ በሆኑበት ቀን፣ የሠረገሎቹ ብረት ያብረቀርቃል፤ የጦሩ ዘንግ ይወዛወዛል።


跟着我们:

广告


广告