Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 22:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 አባቶችና እናቶች በውስጥሽ ተዋረዱ፤ መጻተኞች ተጨቈኑ፤ ድኻ አደጎችና መበለቶች ተንገላቱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አባትንና እናትን አቃለሉ፥ በመካከልሽ መጻተኛውን ጨቆኑ፥ በአንቺ ውስጥ የሙት ልጅንና መበለቲቱን አስጨነቁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 በውስጥሽም አባትና እናት ይናቃሉ፤ የውጪ አገር ሰዎች ይታለላሉ፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶችና አባትና እናት የሌላቸው ልጆች ይበደላሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በአ​ንቺ ውስጥ አባ​ት​ንና እና​ትን አቃ​ለሉ፤ በመ​ካ​ከ​ልሽ በመ​ጻ​ተ​ኛው ላይ በደ​ልን አደ​ረጉ፤ በአ​ንቺ ውስጥ ድሀ አደ​ጉ​ንና መበ​ለ​ቲ​ቱን አስ​ጨ​ነቁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በአንቺ ውስጥ አባትንና እናትን አቃለሉ፥ በመካከልሽ በመጻተኛው ላይ በደልን አደረጉ፥ በአንቺ ውስጥ ድሀ አደጉንና መበለቲቱን አስጨነቁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 22:7
25 交叉引用  

እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህን አደቀቁ፤ ርስትህንም አስጨነቁ።


መበለቲቱንና መጻተኛውን ገደሉ፤ የድኻ አደጉንም ነፍስ አጠፉ።


አባትህንና እናትህን አክብር፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም።


“አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ይገደል።


“መጻተኛውን አትጨቍን፤ በግብጽ መጻተኛ ስለ ነበራችሁ፣ መጻተኛ ምን እንደሚሰማው እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁና።


አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ፣ መብራቱ በድቅድቅ ጨለማ ይጠፋል።


“አባቱን የሚረግም፣ እናቱን የማይባርክ ትውልድ አለ፤


“በአባት ላይ የምታፌዝ ዐይን፣ የእናትንም ትእዛዝ የምትንቅ፣ የሸለቆ ቍራዎች ይጐጠጕጧታል፤ ጆፌ አሞሮችም ይበሏታል።


መልካም ማድረግን ተማሩ፤ ፍትሕን እሹ፣ የተገፉትን አጽናኑ፤ አባት ለሌላቸው ቁሙላቸው፤ ለመበለቶችም ተሟገቱ።


ገዥዎችሽ ዐመፀኞችና የሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ ሁሉም ጕቦን ይወድዳሉ፤ እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤ አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤ የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።


መጻተኛውንና ድኻ አደጉን፣ መበለቲቱንም ባትጨቍኑ፣ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደም ባታፈስሱ፣ የሚጐዷችሁን ሌሎች አማልክት ባትከተሉ፣


ድኻውንና ችግረኛውን ቢጨቍን፣ በጕልበት ቢቀማ፣ በመያዣነት የወሰደውን ባይመልስ፣ ወደ ጣዖታት ቢመለከት፣ አስጸያፊ ተግባራትን ቢፈጽም፣


መሳፍንቷ እያገሣ ግዳዩን እንደሚቦጫጭቅ አንበሳ በውስጧ ያሤራሉ፤ ሕዝቡን ይበላሉ፤ ንብረትንና የከበሩ ነገሮችን ይነጥቃሉ፤ ብዙዎችንም ሴቶች መበለት ያደርጋሉ።


በምድሪቱ የሚኖረው ሕዝብ ይቀማል፤ ይዘርፋል፤ ፍትሕ በማጕደልም ድኻውንና ችግረኛውን ይጨቍናል፤ መጻተኛውንም ይበድላል።


“ ‘አባቱን ወይም እናቱን የሚረግም ማንኛውም ሰው ይገደል፤ አባቱን ወይም እናቱን ረግሟልና ደሙ በራሱ ላይ ነው።


መበለቲቱን ወይም ድኻ አደጉን፣ መጻተኛውን ወይም ድኻውን አታስጨንቁ፤ በልባችሁም አንዳችሁ በአንዳችሁ ላይ ክፉ አታስቡ።’


“ስለዚህ እኔ ለፍርድ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በመተተኞች፣ በአመንዝራዎች፣ በሐሰት በሚምሉ፣ የሠራተኞችን ደመወዝ በሚከለክሉ፣ መበለቶችንና ድኻ አደጉን በሚጨቍኑ፣ መጻተኞችን ፍትሕ በሚነፍጉ፣ እኔንም በማይፈሩት ላይ እመሰክርባቸው ዘንድ እፈጥናለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ሙሴ፣ ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ ይሙት’ ብሎ ነበርና፤


ለመጻተኛው ወይም አባት ለሌለው ልጅ ፍትሕ አትንፈገው፤ የመበለቲቱንም መደረቢያ መያዣ አታድርግ።


“አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።


“በመጻተኛው፣ አባት በሌለውና በመበለቲቱ ላይ ፍትሕ የሚያዛባ የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።


አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንልህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ባዘዘህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር።


跟着我们:

广告


广告