Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 22:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እኔ ልቀጣሽ በምነሣበት ጊዜ፣ በልበ ሙሉነት መቆም ትችያለሽን? ወይስ እጅሽ ሊበረታ ይችላልን? እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ አደርገዋለሁም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከአንቺ ጋር በምነጋገርበት ጊዜ ልብሽ መቋቋም ይችላልን? እጆችሽስ ይጸናሉን? እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ፥ አደርገዋለሁም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እኔ እናንተን በምቀጣበት ጊዜ ወኔ የሚቀርላችሁ ይመስላችኋልን? ወይስ ለመከላከል ኀይል የሚኖራችሁ ይመስላችኋልን? እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ የተናገርኩትንም ቃል እፈጽማለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እኔ በማ​ደ​ር​ግ​ብሽ ወራት ልብሽ ይታ​ገ​ሣ​ልን? ወይስ እጆ​ችሽ ይጸ​ና​ሉን? እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አደ​ር​ገ​ው​ማ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በውኑ እኔ በማደርግብሽ ወራት ልብሽ ይታገሣልን? ወይስ እጅሽ ትጸናለችን? እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ አደርገውማለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 22:14
20 交叉引用  

እንደ እግዚአብሔር ክንድ ያለ ክንድ አለህን? ድምፅህስ እንደ እርሱ ድምፅ ሊያንጐደጕድ ይችላልን?


እንግዲህ ፌዛችሁን አቁሙ፤ አለዚያ እስራታችሁ ይጸናባችኋል፤ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ መላውን ምድር ለማጥፋት ያወጀውን ዐዋጅ ሰምቻለሁ።


ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ እግዚአብሔር እጁን ሲዘረጋ፣ ርዳታ ሰጪው ይሰናከላል፤ ተረጂውም ይወድቃል፤ ሁለቱም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።


“ከዐፈር ሸክላዎች መካከል፣ ከሠሪው ጋራ ክርክር ለሚገጥም ወዮለት! ጭቃ፣ ሸክላ ሠሪውን፣ ‘ምን እየሠራህ ነው?’ ይለዋልን? የምትሠራውስ ሥራ፣ ‘እጅ የለህም’ ይልሃልን?


ልዩ ወዳጆች እንዲሆኑሽ ያስተማርሻቸው፣ ባለሥልጣን ሲሆኑብሽ ምን ትያለሽ? እንደምትወልድ ሴት፣ ምጥ አይዝሽምን?


የዱር ዛፎች ሁሉ ረዥሙን ዛፍ፣ ዝቅ ዝቅ ያለውንም ዛፍ ከፍ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ የለመለመውን ዛፍ አደርቃለሁ፤ ደረቁንም አለመልማለሁ። “ ‘እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ እኔው አደርገዋለሁ።’ ”


እነርሱም፣ ‘ለምን ታቃስታለህ?’ ቢሉህ፣ ‘ስለሚመጣው ክፉ ወሬ ነው፤ ልብ ሁሉ ይቀልጣል፤ እጅም ሁሉ ይዝላል፤ ነፍስ ሁሉ ይደክማል፤ ጕልበትም ሁሉ ውሃ ይሆናል’ በላቸው። እነሆ፤ ይመጣል፤ ይፈጸማልም ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”


ትጠጪዋለሽ፤ ትጨልጪዋለሽም፤ ከዚያም ጽዋውን ትሰባብሪዋለሽ፤ ጡትሽንም ትቈራርጪአለሽ፤ እኔ ተናግሬአለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


“ ‘እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ የምሠራበትም ጊዜ ደርሷል፤ ወደ ኋላ አልልም፤ አልራራም፤ አላመነታምም። እንደ መንገድሽና እንደ ተግባርሽ ይፈረድብሻል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”


ታዲያ በገዳዮችህ ፊት፣ “አምላክ ነኝ” ትላለህን? በገዳዮችህ እጅ ስትገባ፣ አንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።


ከዚያም በዙሪያችሁ የነበሩ የቀሩት አሕዛብ ፈርሶ የነበረውን መልሼ የሠራሁ፣ ጠፍ የነበረውን ያለመለምሁ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ እኔም አደርገዋለሁ።’


“ከዚያም ቍጣዬ ይበርዳል፤ በእነርሱ ላይ የመጣው መቅሠፍቴ ይመለሳል፤ ስበቀላቸው እረካለሁ፤ በእነርሱም ላይ መዓቴን ካወረድሁ በኋላ፣ እኔ እግዚአብሔር በቅናት እንደ ተናገርሁ ያውቃሉ።


እነርሱም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ ይህንም ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁ ብዬ የተናገርሁት በከንቱ አይደለም።


እጅ ሁሉ ይዝላል፤ ጕልበት ሁሉ ውሃ ይሆናል።


በሰራዊቱ ፊት፣ እግዚአብሔር ያንጐደጕዳል፤ የሰራዊቱ ብዛት ስፍር ቍጥር የለውም፤ ትእዛዙንም የሚያደርግ እርሱ ኀያል ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ፣ እጅግም የሚያስፈራ ነው፤ ማንስ ሊቋቋመው ይችላል?


እርሱ የሚመጣበትን ቀን ማን ሊቋቋመው ይችላል? በሚገለጥበትስ ጊዜ በፊቱ መቆም የሚችል ማን ነው? እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳት ወይም እንደ ልብስ ዐጣቢ ሳሙና ነውና።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ቃሌ ግን አያልፍም።


ጌታን እናስቀናውን? በብርታትስ ከርሱ እንበልጣለንን?


በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ እጅግ የሚያስፈራ ነው።


የእስራኤል ክብር የሆነው እግዚአብሔር አይዋሽም፤ አይጸጸትምም፤ እርሱ ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለምና።”


跟着我们:

广告


广告