Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 20:47 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 ለደቡቡ ደን እንዲህ በል፤ ‘የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በአንተ ላይ እሳት ልለኵስ ነው፤ እሳቱ የለመለመውንና የደረቀውን ዛፍህን ሁሉ ይበላል፤ የሚንቦገቦገው ነበልባሉም አይጠፋም፤ ከደቡብ እስከ ሰሜን ያለውን ፊት ሁሉ ይለበልባል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 ለደቡብም ዱር፦ የጌታን ቃል ስማ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በአንተ ውስጥ እሳት አነድዳለሁ፤ በውስጥህም ያለውን የለመለመውንና የደረቀውን ዛፍ ሁሉ ይበላል፤ የሚቃጠል ነበልባል አይጠፋም፤ ከደቡብም ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ፊት ሁሉ ይቃጠልበታል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 ለደቡብም ጫካ እኔ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ የሚለውን ስማ ብለህ ንገረው፤ ‘ተመልከት! እነሆ እኔ በውስጥህ እሳትን በማቀጣጠል ላይ ነኝ፤ ይህም እሳት ለምለሙንም ሆነ ደረቁን ሳይመርጥ ዛፎችን ሁሉ ያቃጥላል፤ እሳቱንም ሊያጠፋው የሚችል አይኖርም፤ ከደቡብ እስከ ሰሜን ይዛመታል፤ በመንገዱ ያገኘውን ሁሉ ያቃጥላል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 ለና​ጌ​ብም ዱር እን​ዲህ በለው፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በአ​ንተ ውስጥ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በው​ስ​ጥ​ህም ያለ​ውን የለ​መ​ለ​መ​ው​ንና የደ​ረ​ቀ​ውን ዛፍ ሁሉ ይበ​ላል፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም ነበ​ል​ባል አይ​ጠ​ፋም፤ ከደ​ቡ​ብም ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ፊት ሁሉ ይቃ​ጠ​ል​በ​ታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 ለደቡብም ዱር፦ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በአንተ ውስጥ እሳት አነድዳለሁ፥ በውስጥህም ያለውን የለመለመውንና የደረቀውን ዛፍ ሁሉ ይበላል፥ የሚቃጠል ነበልባል አይጠፋም፥ ከደቡብም ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ፊት ሁሉ ይቃጠልበታል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 20:47
20 交叉引用  

ሽብር ይይዛቸዋል፤ ሥቃይና ጭንቀት ይደርስባቸዋል፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ያምጣሉ፤ እርስ በርሳቸው በድንጋጤ ይተያያሉ፤ ፊታቸውም በፍርሀት ቀይ ይሆናል።


ከቀድሞ ጀምሮ ቶፌት የተባለ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅቷል፤ ለንጉሡም ተበጅቷል፤ ማንደጃ ጕድጓዱም ሰፊና ጥልቅ ነው፤ በውስጡም ብዙ እሳትና ማገዶ አለ፤ የእግዚአብሔርም እስትንፋስ እንደ ፈሳሽ ድኝ ያቀጣጥለዋል።


“ወጥተውም በእኔ ላይ ያመፁትን ሰዎች ሬሳ ያያሉ፤ የሚበሏቸው ትሎች አይሞቱም፤ የሚያቃጥላቸው እሳታቸው አይጠፋም፤ ለሰውም ዘር ሁሉ አስጸያፊ ይሆናሉ።”


ነገር ግን የሰንበትን ቀን ሳትቀድሱ፣ በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች በመግባት ትእዛዜን ብትጥሱ፣ በኢየሩሳሌም በሮች ላይ ምሽጎቿን የሚበላ፣ የማይጠፋ እሳት እጭራለሁ።’ ”


የዳዊት ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ካደረጋችሁት ክፋት የተነሣ፣ ቍጣዬ እንዳይቀጣጠል፣ ማንም ሊያጠፋው እስከማይችል እንዳይነድድ፣ በየማለዳው ፍትሕን አድርጉ፤ የተበዘበዘውን ሰው፣ ከጨቋኙ እጅ አድኑት።


እንደ ሥራችሁ መጠን እቀጣችኋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በዱሯም እሳት እለኵሳለሁ፤ በዙሪያዋ ያለውንም ሁሉ ይበላል።’ ”


“ ‘አንቺ አመንዝራ ሆይ፤ እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ!


የዱር ዛፎች ሁሉ ረዥሙን ዛፍ፣ ዝቅ ዝቅ ያለውንም ዛፍ ከፍ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ የለመለመውን ዛፍ አደርቃለሁ፤ ደረቁንም አለመልማለሁ። “ ‘እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ እኔው አደርገዋለሁ።’ ”


ከዋና ቅርንጫፎቿ ከአንዱ እሳት ወጣ፤ ፍሬዋንም በላ። በትረ መንግሥት የሚሆን፣ አንድም ጠንካራ ቅርንጫፍ አልተረፈም።’ ይህ ሙሾ ነው፤ ለሐዘን እንጕርጕሮም ይሆናል።”


የተሳለው ሊገድል፣ የተወለወለውም እንደ መብረቅ ሊብረቀረቅ ነው! “ ‘ታዲያ፣ እንዴት ደስ ሊለን ይችላል? ሰይፉ የልጄን በትረ መንግሥት እንደ ማንኛውም በትር ንቋል።


ለእሳት ማገዶ ትሆናለህ፣ ደምህ በምድርህ ይፈስሳል፣ ከእንግዲህ መታሰቢያ አይኖርህም፤ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁና።’ ”


ከመንጋው ሙክቱን ውሰድ፤ ዐጥንቱን ለማብሰል ብዙ ማገዶ ከሥሩ ጨምር፤ ሙክክ እስከሚል ቀቅለው፤ ዐጥንቱም ይብሰል።


እንግዲህ በርጥብ ዕንጨት እንዲህ ካደረጉ፣ በደረቁ ምን ያደርጉ ይሆን?”


በቍጣዬ እሳት ተቀጣጥሏልና፤ እርሱ እስከ ሲኦል ዘልቆ ይነድዳል። ምድርን እስከ ሰብሏ ይበላል፤ የተራሮችንም መሠረት ያቀጣጥላል።


跟着我们:

广告


广告