Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 20:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ምክንያቱም ሥርዐቴን አቃለሉ፤ ሰንበቴን አረከሱ እንጂ ሕጌን አልጠበቁም፤ ዐይናቸውም ከአባቶቻቸው ጣዖታት ጋራ ተጣብቋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ሥርዓቴንም ጥሰዋልና፤ ሰንበታቴንም አርክሰዋልና፤ ዓይናቸውም የአባቶቻቸውን ጣዖታቶች ተከትለዋልና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ይህንንም ያደረግኹት ሕጌን ስለ ተላለፉ፥ ሥርዓቴንም ስላልተከተሉ፥ ሰንበትን ስላረከሱ፥ የቀድሞ አባቶቻቸውንም ጣዖቶች ስለ አመለኩ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ፍር​ዴን አላ​ደ​ረ​ጉ​ምና፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንም ጥሰ​ዋ​ልና፥ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋ​ልና፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ዐሳብ ተከ​ት​ለ​ዋ​ልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ሥርዓቴንም ጥሰዋልና፥ ሰንበታቴንም አርክሰዋልና፥ ዓይናቸውም የአባቶቻቸውን ጣዖታቶች ተከትለዋልና።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 20:24
11 交叉引用  

እኔ፣ ፍሬዋንና በረከቷን እንድትበሉ፣ ለም ወደ ሆነ መሬት አመጣኋችሁ፤ እናንተ ግን መጥታችሁ ምድሬን አረከሳችሁ፤ ርስቴንም ጸያፍ አደረጋችሁ።


ድኻውንና ችግረኛውን ቢጨቍን፣ በጕልበት ቢቀማ፣ በመያዣነት የወሰደውን ባይመልስ፣ ወደ ጣዖታት ቢመለከት፣ አስጸያፊ ተግባራትን ቢፈጽም፣


“በኰረብታ መስገጃ የቀረበውን ባይበላ፣ በእስራኤል ቤት ወዳሉት ጣዖታት ባይመለከት፣ የባልንጀራውን ሚስት ባያባልግ፣


በኰረብታ ባሉ አብያተ ጣዖት የቀረበውን አይበላም፤ በእስራኤል ቤት ወዳሉት ጣዖታት አይመለከትም የባልንጀራውን ሚስት አያባልግም፤ ከሴት ጋራ በወር አበባዋ ጊዜ አይተኛም።


“ ‘ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ በምድረ በዳ ዐመፀብኝ፤ ሰው ቢጠብቀው በሕይወት የሚኖርበትን ሥርዐቴን አልጠበቁም፤ ሕጌንም ተላለፉ፤ ሰንበቴንም ፈጽሞ አረከሱ። እኔም መዓቴን ላፈስስባቸው፣ በምድረ በዳም ላጠፋቸው ወስኜ ነበር።


ምክንያቱም ሕጎቼን ተላልፈዋል፤ ሥርዐቴን አልጠበቁም፤ ሰንበቴንም አርክሰዋል፤ ልባቸው ከጣዖቶቻቸው ጋራ ተጣብቋልና።


ደግሞም ይህን አደረጉብኝ፤ በዚያ ቀን ቤተ መቅደሴን አረከሱ፤ ሰንበታቴንም አቃለሉ።


እነዚህ ከሰይፍ የተረፉት፣ ከእኔ ዘወር ባለ አመንዝራ ልባቸውና ጣዖትን በተከተለ አመንዝራ ዐይናቸው የቱን ያህል እንዳሳዘኑኝ፤ በአሕዛብ ምድር ሆነው ያስታውሱኛል፤ ካደረጉት ክፋትና ከፈጸሙት ርኩስ ተግባር ሁሉ የተነሣም ራሳቸውን ይጸየፋሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የይሁዳ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋል፤ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፤ አባቶቻቸው በተከተሏቸው አማልክት፣ በሐሰት አማልክት በመመራት ስተዋልና።


ወደ ሰማይ ቀና ብለህ ፀሓይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን፣ የሰማይ ሰራዊትንም ሁሉ በምትመለከትበት ጊዜ፣ ወደ እነርሱ እንዳትሳብና እንዳትሰግድላቸው፣ አምላክህ እግዚአብሔር ከሰማይ በታች ላሉ ሕዝቦች ሁሉ ድርሻ አድርጎ የሰጣቸውንም ነገሮች እንዳታመልክ ተጠንቀቅ።


跟着我们:

广告


广告