Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 16:57 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

57 ይህም ኀጢአትሽ ከመገለጡ በፊት ነበር። አሁን ግን በዙሪያሽ ሆነው ለሚንቁሽ ለኤዶም ሴት ልጆችና ለጎረቤቶቿ ሁሉ፣ እንዲሁም ለፍልስጥኤም ሴት ልጆች መሣለቂያ ሆነሻል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

57 ክፋትሽ ሳይገለጥ በፊት፤ አሁን ለአራም ሴቶች ልጆችና ለጎረቤቶችዋ ሁሉ፥ በዙሪያሽም ላሉት ለሚንቁሽ ለፍልስጥኤም ሴቶች ልጆች እንደ እርሷ መሰደቢያ ሆነሻል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

57 ይህንንስ ያደረግሽው የአንቺ በደል ከመታወቁ በፊት አይደለምን? አሁን ግን አንቺ ለሶርያ ከተሞችና ለጐረቤቶቻቸው እንዲሁም ለፍልስጥኤም ከተሞችና ባካባቢው ላሉ ለሚንቁሽ ሁሉ መሳለቂያ ሆነሻል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

57 ክፋ​ትሽ እንደ ዛሬው ሳይ​ገ​ለጥ ለሶ​ርያ ሴቶች ልጆ​ችና ለጐ​ረ​ቤ​ቶ​ችዋ ሁሉ በዙ​ሪ​ያ​ሽም ለሚ​ከ​ቡሽ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያት ሴቶች ልጆች መሰ​ደ​ቢያ ሆነ​ሻል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

57 አሁን ለሶርያ ሴቶች ልጆችና ለጎረቤቶችዋ ሁሉ፥ በዙሪያሽም ለሚንቁሽ ለፍልስጥኤም ሴቶች ልጅች እንደ እርስዋ መሰደቢያ ሆነሻል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 16:57
24 交叉引用  

ይህን አድርገህ ዝም አልሁ፤ እንደ አንተ የሆንሁ መሰለህ። አሁን ግን እገሥጽሃለሁ፣ ፊት ለፊትም እወቅሥሃለሁ።


ንጉሡ አካዝ በሞተበት ዓመት እንዲህ የሚል ንግር መጣ፤


የዖዝያን የልጅ ልጅ፣ የኢዮአታም ልጅ አካዝ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ዘመን፣ የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የእስራኤል ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፤ ነገር ግን ድል ሊያደርጓት አልቻሉም።


“ይህ ሕዝብ፣ ‘እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሁለቱን መንግሥታት ጥሏል’ እንደሚሉ አላስተዋልህምን? ሕዝቤን ንቀዋል፤ እንደ ሕዝብም አልቈጠሯቸውም።


የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ቅጣትሽ ያበቃል፤ እርሱም የስደትሽን ዘመን አያራዝምም፤ ነገር ግን አንቺ የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፤ ኀጢአትሽን ይቀጣል፤ ክፋትሽንም ይፋ ያወጣል።


ስለዚህ ክንዴን በአንቺ ላይ አንሥቼ ድርጎሽን ቀነስሁ፤ ከክፉ መንገድሽም የተነሣ በብልግናሽ ለሚያፍሩ ጠላቶችሽ ለፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች አሳልፌ ሰጠሁሽ።


በታበይሽበት ወቅት የእኅትሽን የሰዶምን ስም ለመጥራት እንኳ ፈቃደኛ አልነበርሽም፤


“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እናንተ በምታደርጉት ሁሉ ኀጢአታችሁን በመግለጽ፣ በግልጽም በማመፅ በደላችሁን ስላሳሰባችሁ፣ እንዲህም ስላደረጋችሁ በምርኮ ትወሰዳላችሁ።


ባፈሰስሽው ደም በድለሻል፤ በሠራሽውም ጣዖት ረክሰሻል፤ ከዚህም የተነሣ ቀንሽን አቅርበሻል፤ ዕድሜሽንም አሳጥረሻል። ስለዚህ ለአሕዛብ መዘባበቻ፣ ለአገሩም ሁሉ መሣለቂያ አደርግሻለሁ።


“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰፊና ጥልቅ የሆነውን ጽዋ፣ የእኅትሽን ጽዋ ትጠጪአለሽ፤ ብዙም ስለሚይዝ ስድብና ነቀፌታ ትጠግቢአለሽ።


“ ‘ምርትሽ ብዙ እንደ መሆኑ፣ ሶርያ ከአንቺ ጋራ ትገበያይ ነበር፤ ሸቀጥሽንም በበሉር፣ በሐምራዊ ጨርቅ፣ በወርቀ ዘቦ፣ በጥሩ በፍታ፣ በዛጐልና በቀይ ዕንቍ ይለውጡ ነበር።


“በዙሪያሽ ባሉ አሕዛብ መካከል፤ በአጠገብሽም በሚያልፉ ሁሉ ፊት ባድማና መሣለቂያ አደርግሻለሁ።


በቍጣና በመዓት፣ እንዲሁም በጭካኔ ፍርድ በማመጣብሽ ጊዜ፣ በዙሪያሽ ባሉ አሕዛብ ዘንድ የመሣቂያና የመሣለቂያ፣ የተግሣጽና የማስደንገጫ ምልክት ትሆኛለሽ። እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።


አሁንም በውሽሞቿ ፊት፣ ነውሯን እገልጣለሁ፤ ከእጄም የሚያድናት የለም።


እስራኤልን በምፈውስበት ጊዜ፣ የኤፍሬም ኀጢአት፣ የሰማርያም ክፋት ይገለጣል። እነርሱ ያጭበረብራሉ፤ ሌቦች ቤቶችን ሰብረው ይገባሉ፤ ወንበዴዎችም በየመንገድ ይዘርፋሉ።


በዚያ ጊዜ፣ ያስጨነቁሽን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዐንካሶችን እታደጋለሁ፤ የተበተኑትንም እሰበስባለሁ፤ በተዋረዱበት ምድር ሁሉ፣ ለውዳሴና ለክብር አደርጋቸዋለሁ።


ከዚያም በለዓም ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤ “ባላቅ ከአራም አመጣኝ፣ የሞዓብ ንጉሥ ከምሥራቅ ተራሮች። ‘ና ያዕቆብን ርገምልኝ፤ መጥተህም እስራኤልን አውግዝልኝ’ አለኝ።


ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ በምንም ነገር አትፍረዱ፤ ጌታ እስኪመጣ ጠብቁ። እርሱ በጨለማ ውስጥ የተሰወረውን ወደ ብርሃን ያመጣዋል፤ በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውንም ሐሳብ ይገልጠዋል። በዚያ ጊዜ እያንዳንዱ ሰው የሚገባውን ምስጋና ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።


跟着我们:

广告


广告