ሕዝቅኤል 16:34 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም34 ስለዚህ ያንቺ ግልሙትና ከሌሎቹ የተለየ ነው፤ ማመንዘር የሚሻ ማንም ሰው፣ አንቺን አሳድዶ ማግባባት አያስፈልገውም። ዋጋ ትከፍያለሽ እንጂ አይከፈልሽም፤ አንቺ የሌሎች ፍጹም ተቃራኒ ነሽ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)34 አመንዝራነትሽ ከሌሎች ሴቶች የተለየ ነው፥ ማንም ለዝሙት የሚከተልሽ የለም፤ ማንም ዋጋ ሳይሰጥሽ አንቺ ዋጋ ትሰጫለሽ፤ የተለየሽም ሆንሽ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም34 ስለዚህም አንቺ ልዩ ዐይነት አመንዝራ ሴት ሆነሻል። ነገር ግን እንደዚህ እንድትሆኚ ያባበለሽ የለም፤ ገንዘብ ትከፍያቸዋለሽ እንጂ የሚከፍልሽ የለም፤ ስለዚህ በእርግጥ በአመንዝራነትሽ አንቺ ልዩ ነሽ።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)34 ዝሙትሽ ከሌሎች ሴቶች ዝሙት ልዩ ነው፤ ማንም ለዝሙት የሚከተልሽ የለም፤ ዋጋ ሳይሰጥሽ አንቺ ዋጋ በመስጠትሽ በዚህ ነገር ልዩ ሆነሻል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)34 ግልሙትናሽ ከሌሎች ሴቶች ግልብጥ ነው፥ ማንም ለግልሙትና የሚከተልሽ የለም፥ ዋጋ ሳይሰጥሽ አንቺ ዋጋ በመስጠትሽ በዚህ ነገር ልዩ ሆነሻል። 参见章节 |