ሕዝቅኤል 16:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ወርቀ ዘቦ አለበስሁሽ፤ ምርጥ ቈዳ ጫማም አደረግሁልሽ፤ ያማረ በፍታ አለበስሁሽ ውድ መደረቢያም አጐናጸፍሁሽ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ወርቀ ዘቦም አለበስሁሽ፥ ከጥሩ ቆዳ የተሠራ ጫማ አደረግሁልሽ፥ በጥሩ በፍታ አስታጠቅሁሽ፥ ውድ መደረቢያም ደረብሁልሽ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ጥበብ ቀሚስ አለበስኩሽ፤ ከምርጥ ቆዳ የተሠራ ጫማ አደረግሁልሽ፤ ሐር ሻሽ በራስሽ ላይ አሰርኩልሽ፤ ውድ የሆነ ካባ ደረብኩልሽ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ወርቀ ዘቦም አለበስሁሽ፤ ጥቁር ጫማም አደረግሁልሽ፤ በጥሩ በፍታ አስታጠቅሁሽ፤ በሐርም ከደንሁሽ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ወርቀ ዘቦም አለበስሁሽ በአቆስጣ ቁርበትም ጫማ አደረግሁልሽ፥ በጥሩ በፍታ አስታጠቅሁሽ በሐርም ከደንሁሽ። 参见章节 |