Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 13:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “ ‘ሰላም ሳይኖር፣ “ሰላም አለ” እያሉ ሕዝቤን ያስታሉ፤ ሕዝቡ ካብ ሲሠራ እነርሱ በኖራ ይለስናሉ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ምክንያቱም ሰላም ሳይኖር ሰላም እያሉ ሕዝቤን አታልለዋልና፥ አንድ ሰው ቅጥር ሲሠራ፥ እነሆ በኖራ ይቀቡታል፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “እነዚህ ነቢያት የማይታመኑ ሆኑ፤ ሰላም በሌለበት ሰላም አለ ብለው ለሕዝቤ ይናገራሉ፤ የዘመመ ግድግዳን ቀለም በመቀባት ያደሱ የሚመስላቸው ሠራተኞችን ይመስላሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሰላም ሳይ​ኖር፦ ሰላም እያሉ ሕዝ​ቤን አታ​ል​ለ​ዋ​ልና፤ አን​ዱም ሰው ቅጥር ሲሠራ እነ​ርሱ ያለ​ገ​ለባ ይመ​ር​ጉ​ታል፤ ይወ​ድ​ቃ​ልም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ሰላም ሳይኖር፦ ሰላም እያሉ ሕዝቤን አታልለዋልና፥ አንዱም ሰው ቅጥር ሲሠራ፥ እነሆ፥

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 13:10
27 交叉引用  

ሕዝቡ ግን አልሰሙም፤ እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ፊት ካጠፋቸው አሕዛብ የባሰ ክፉ ድርጊት እንዲፈጽሙ ምናሴ አሳታቸው።


ሚክያስን ሊጠራ ሄዶ የነበረውም መልእክተኛ፣ “እነሆ፣ ሌሎቹ ነቢያት በአንድ አፍ ሆነው፣ ለንጉሡ መልካምን ነገር እየተነበዩ ነው፤ እባክህ የአንተም ቃል እንደ ቃላቸው ይሁን፤ ንጉሡን ደስ የሚያሠኘውን ተናገር” አለው።


ጻድቅ ሰው ለወዳጁ መልካም ምክር ይሰጣል፤ የክፉዎች መንገድ ግን ወደ ስሕተት ይመራቸዋል።


ባለራእዮችን፣ “ከእንግዲህ ራእይን አትዩ!” ይላሉ፤ ነቢያትንም እንዲህ ይላሉ፤ “እውነተኛውን ትንቢት ከእንግዲህ አትንገሩን፤ ደስ የሚያሠኘውን ንገሩን፤ የሚያማልለውን ተንብዩልን።


አምላኬ፣ “ለክፉዎች ሰላም የላቸውም” ይላል።


እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ወዮ! ነቢያቱ ‘ሰይፍ አታዩም፤ ራብም አያገኛችሁም፤ ነገር ግን በዚህ ስፍራ ዘለቄታ ያለው እውነተኛ ሰላም እሰጣችኋለሁ’ ይላል ይሏቸዋል” አልሁ።


እኔን ለሚንቁኝ፣ ‘እግዚአብሔር ሰላም ይሆንላችኋል ብሏል’ ይላሉ፤ የልባቸውን እልኸኝነት ለሚከተሉም ሁሉ፣ ‘ክፉ ነገር አይነካችሁም’ ይሏቸዋል።


“እነሆ፤ ሐሰተኛ ሕልም ተመርኵዘው ትንቢት የሚናገሩትን ነቢያት እቃወማለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “እኔ ሳልልካቸው ወይም ሳልሾማቸው ደፍረው ውሸት ይናገራሉ፤ ሕዝቤንም ያስታሉ፤ ለዚህም ሕዝብ አንዳች አይረቡትም” ይላል እግዚአብሔር።


ነገር ግን ስለ ሰላም ትንቢት የተናገረ ነቢይ እግዚአብሔር በእውነት እንደ ላከው የሚታወቀው የተናገረው ትንቢት ሲፈጸም ነው።”


እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰይፍ ዐንገታቸው ላይ ተቃጥቶ ሳለ፣ ‘ሰላም ይሆንላችኋል’ ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን ለምን እጅግ አታለልህ?” አልሁ።


ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናት በነቢያቱ ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ይወድዳሉ፤ ፍጻሜው ሲደርስ ግን ምን ታደርጉ ይሆን?”


“ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል፤ እረኞቻቸው አሳቷቸው፤ በተራሮችም ላይ እንዲቅበዘበዙ አደረጓቸው፤ በተራራና በኰረብታ ላይ ተንከራተቱ፤ ማደሪያቸውንም ረሱ።


የሕዝቤን ቍስል እንደ ቀላል ቈጠሩ፣ እንዲፈወስም ተገቢውን እንክብካቤ አላደረጉለትም፤ ሰላምም ሳይኖር፣ ‘ሰላም፣ ሰላም’ ይላሉ።


የሕዝቤን ቍስል ብርቱ እንዳይደለ በመቍጠር፣ የተሟላ ፈውስ ሳይኖር እንዲሁ ያክማሉ፤ ሰላም ሳይኖር፣ “ሰላም፣ ሰላም” ይላሉ።


ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ መልካም ነገር ግን አልመጣም፤ የፈውስ ጊዜን ተመኘን፤ ነገር ግን ሽብር ብቻ ሆነብን።


ኢየሩሳሌም ትንቢት የተናገሩላትና ሰላም ሳይኖር የሰላም ራእይ ያዩላት የእስራኤል ነቢያት ጠፍተዋል፣ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።” ’


ነቢያቷም በሐሰት ራእይና በውሸት ሟርት ይህን ሁሉ ድርጊት ያድበሰብሱላቸዋል፤ እግዚአብሔርም ሳይናገር፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል’ ይላሉ።


ሽብር በመጣ ጊዜ ሰላምን ይሻሉ፤ ነገር ግን አያገኟትም።


የቅጣት ቀን መጥቷል፤ የፍርድም ቀን ቀርቧል፤ እስራኤልም ይህን ይወቅ! ኀጢአታችሁ ብዙ፣ ጠላትነታችሁም ታላቅ ስለ ሆነ፣ ነቢዩ እንደ ቂል፣ መንፈሳዊውም ሰው እንደ እብድ ተቈጥሯል።


ሐሰተኛና አታላይ ሰው መጥቶ፣ ‘ስለ ብዙ የወይን ጠጅና ስለሚያሰክር መጠጥ ትንቢት እነግራችኋለሁ’ ቢል፣ ለዚህ ሕዝብ ተቀባይነት ያለው ነቢይ ይሆናል።


አሁን ግን ትዕቢተኞችን ቡሩካን እንላቸዋለን፤ ክፉ አድራጊዎች ይበለጽጋሉ፤ እግዚአብሔርን የሚፈታተኑትም ያመልጣሉ።’ ”


ሰዎች፣ “ሰላምና ደኅንነት ነው” ሲሉ፣ ምጥ እርጉዝ ሴትን እንደሚይዛት እንዲሁ ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።


በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች እምነትን ክደው አታላይ መናፍስትንና የአጋንንትን ትምህርት እንደሚከተሉ መንፈስ በግልጽ ይናገራል።


ክፉዎችና አታላዮች ግን እየሳቱና እያሳቱ፣ በክፋትም ላይ ክፋት እየጨመሩ ይሄዳሉ።


ስለሚያስቷችሁ ሰዎች ይህን ጽፌላችኋለሁ።


ይሁን እንጂ የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ ነቢይ ነኝ የምትለዋን ሴት ኤልዛቤልን ችላ ብለሃታል፤ እርሷ ባሮቼ እንዲሴስኑና ለጣዖት የተሠዋ ምግብ እንዲበሉ በትምህርቷ ታስታቸዋለች።


跟着我们:

广告


广告