Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 12:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 “የሰው ልጅ ሆይ፤ የእስራኤል ቤት፣ ‘ይህ ሰው የሚያየው ራእይ ገና ለሩቅ ዘመን የሚሆን ነው፤ የሚናገረውም ትንቢት የረዥም ጊዜ ትንቢት ነው’ ይላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ የእስራኤል ቤት እንዲህ ይላሉ፦ የሚያየው ራእይ ለብዙ ዘመን ነው፥ እርሱም ለሩቅ ወራት ትንቢት ይናገራል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 “የሰው ልጅ ሆይ! እስራኤላውያን የአንተ ራእይና ትንቢት ‘ከብዙ ዘመን በኋላ የሚፈጸም ነው’ ብለው ይናገራሉ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 “የሰው ልጅ ሆይ! ዐመ​ፀ​ኛው የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት፦ ይህቺ የሚ​ያ​ያት ራእይ ለብዙ ዘመን ናት፤ እር​ሱም ለሩቅ ወራት ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ራል” ይላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ፥ የእስራኤል ቤት፦ ይህች የሚያያት ራእይ ለብዙ ዘመን ናት፥ እርሱም ለሩቅ ወራት ትንቢት ይናገራል ይላሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 12:27
8 交叉引用  

“የሰው ልጅ ሆይ፤ በእስራኤል ምድር፣ ‘ዘመኑ ረዝሟል፤ ራእዩ ሁሉ ከንቱ ሆኗል’ የምትሉት ይህ አባባል ምንድን ነው?


ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤


“ስለዚህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከተናገርሁት ቃል ከእንግዲህ የሚዘገይ የለም፤ የምለው ሁሉ ይፈጸማል ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”


ራእዩ ሊፈጸም ገና ብዙ ዘመን ስለሚቀረው፣ ወደ ፊት በሕዝብህ ላይ የሚሆነውን ልገልጽልህ አሁን ወደ አንተ መጥቻለሁ።”


“የተሰጠህ የምሽቱና የማለዳው ራእይ እውነት ነው፤ ነገር ግን ከብዙ ዘመን በኋላ የሚሆነውን ስለሚያመለክት ራእዩን ዝጋው።”


ክፉውን ቀን ለምታርቁ፣ የግፍንም ወንበር ለምታቀርቡ ወዮላችሁ!


እነርሱም፣ “ ‘እመጣለሁ’ ያለው ታዲያ የት አለ? አባቶች ከሞቱበት ከፍጥረት መጀመሪያ አንሥቶ እስካሁን ድረስ ሁሉም ነገር እንዳለ ይኖራል” ይላሉ።


跟着我们:

广告


广告