Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 12:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ‘እኔ ምልክታችሁ ነኝ’ በላቸው። “እኔ እንዳደረግሁት፤ እንዲሁ በእነርሱ ይደረግባቸዋል፤ በምርኮኛነትም ተሰድደው ይሄዳሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እንዲህም በላቸው፦ እኔ ምልክታችሁ ነኝ፥ እኔ እንዳደረግሁት እንዲሁ ይደረግባቸዋል፥ እነርሱም ወደ ስደት ወደ ምርኮ ይሄዳሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ይህም አንተ ያደረግኸው ነገር ሁሉ በእነርሱ ላይ ሊፈጸም ለተቃረበው ነገር ምልክት መሆኑን አስታውቃቸው፤ እነርሱም ስደተኞችና ምርኮኞች ይሆናሉ ማለት ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ደግ​ሞም፦ እኔ ምል​ክ​ታ​ችሁ ነኝ፤ እኔ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እን​ዲሁ ይደ​ረ​ግ​ባ​ቸ​ዋል፥ እነ​ር​ሱ​ንም ማር​ከው ይወ​ስ​ዷ​ቸ​ዋል በል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ደግሞም፦ እኔ ምልክታችሁ ነኝ፥ እኔ እንዳደረግሁ እንዲሁ ይደረግባቸዋል፥ እነርሱም በስደት ወደ ምርኮ ይሄዳሉ በል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 12:11
11 交叉引用  

የክብር ዘቡ አዛዥ ናቡዘረዳን ድኾችንና በከተማዪቱ የቀረውን ሕዝብና ሸሽተው ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን አፈለሳቸው።


ሴዴቅያስ ዐይኑ እያየም ወንዶች ልጆቹን ገደሉበት፤ ከዚያም ሁለት ዐይኖቹን በማውጣት በናስ ሰንሰለት አስረው ወደ ባቢሎን ወሰዱት።


አንቺ የተከበብሽ፤ ከያለበት ንብረትሽን ሰብስቢ፤


እነርሱም፣ ‘ወዴት እንሂድ?’ ቢሉህ፣ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ለሞት የተመደበ ወደ ሞት፣ ለሰይፍ የተመደበ ወደ ሰይፍ፣ ለራብ የተመደበ ወደ ራብ፣ ለምርኮ የተመደበ ወደ ምርኮ ይሄዳል።’


የክብር ዘቡ አዛዥ ናቡዘረዳን አንዳንድ የድኻ ድኾችንና በከተማዪቱ የቀረውን ሕዝብና ሸሽተው ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን ሰዎች ከእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ጋራ አፈለሳቸው።


“ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፤ እነርሱ እያዩህ በቀን ጓዝህን ጠቅልለህ ለመሰደድ ተዘጋጅ፤ ካለህበትም ስፍራ ተነሥተህ ወደ ሌላ ቦታ ሂድ፤ ዐመፀኛ ቤት ቢሆኑም ምናልባት ይህን ያስተውሉታል።


በፊታቸው ጓዝህን በትከሻህ ላይ አስቀምጥ፣ በምሽትም ተሸክመህ ውጣ። ለእስራኤል ቤት ምልክት አድርጌሃለሁና ምድሪቱን እንዳታይ ፊትህን ሸፍን።”


“አንተ፣ የሰው ልጅ ሆይ፤ አንድ የሸክላ ጡብ ወስደህ ከፊት ለፊትህ አስቀምጥ፤ የኢየሩሳሌምን ከተማ ካርታ ሥራበት።


የብረት ምጣድ ወስደህ በአንተና በከተማዪቱ መካከል እንደ ብረት ቅጥር አቁመው፤ ፊትህንም ወደ እርሷ አዙር፤ የተከበበች ትሆናለች፤ አንተም ትከብባታለህ። ይህም ለእስራኤል ቤት ምልክት ይሆናል።


“ ‘ሊቀ ካህኑ ኢያሱ ሆይ፤ ስማ፤ በፊትህ የሚቀመጡትም ረዳቶችህ ገና ወደ ፊት ለሚመጡት ምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ፤ እነሆ፤ ባሪያዬን ቍጥቋጡን አመጣለሁ።


跟着我们:

广告


广告