Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 10:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ሰውየው ወደ ውስጥ በገባ ጊዜ፣ ኪሩቤል በቤተ መቅደሱ ውስጥ በደቡብ በኩል ቆመው ነበር፤ ደመናም ውስጠኛውን አደባባይ ሞላ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሰውዬው ሲገባ ኪሩቤል በቤቱ በደቡብ በኩል ቆመው ነበር፥ ደመናውም ውስጠኛውን አደባባይ ሞላው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ወደ ውስጥ በሚገባበትም ጊዜ ኪሩቤል ከቤተ መቅደሱ በስተ ደቡብ በኩል ቆመው ነበር፤ በውስጥ በኩል ያለውንም አደባባይ ደመና ሞላው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሰው​የ​ውም ሲገባ ኪሩ​ቤል በቤቱ ቀኝ በኩል ቆመው ነበር፤ ደመ​ና​ውም ውስ​ጠ​ኛ​ውን አደ​ባ​ባይ ሞላ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሰውዬውም ሲገባ ኪሩቤል በቤቱ ቀኝ በኩል ቆመው ነበር፥ ደመናውም ውስጠኛውን አደባባይ ሞላ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 10:3
7 交叉引用  

ሰውንም ካስወጣው በኋላ፣ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና በየአቅጣጫው የምትገለባበጥ ነበልባላዊ ሰይፍ ከዔድን በስተምሥራቅ አኖረ።


በስርየት መክደኛው ዳርና ዳር ላይ የሚሆኑ ከወርቅ የተቀረጹ ሁለት ኪሩቤል ሥራ።


የእግዚአብሔር ክብር ለምሥራቅ ትይዩ በሆነው በር ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ።


“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ለምሥራቅ ትይዩ የሆነው የውስጠኛው አደባባይ በር በስድስቱ የሥራ ቀኖች ይዘጋ፤ ነገር ግን በሰንበት ቀንና በወር መባቻ ቀን ይከፈት።


ደግሞም ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፤ እነሆም በመተላለፊያውና በመሠዊያው መካከል በቤተ መቅደሱ መግቢያ ላይ ሃያ ዐምስት ሰዎች ያህል ነበሩ፤ ጀርባቸውን ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣ ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ አድርገው ለምትወጣዋ ፀሓይ ይሰግዱ ነበር።


እርሱም እጅ መሳይ ዘርግቶ የራስ ጠጕሬን ያዘ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል አነሣኝ፤ እርሱም ቅናት የሚያነሣው ጣዖት ወደ ቆመበት፣ ወደ ውስጠኛው አደባባይ መግቢያ ወደ ሰሜን በር ወደ ኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ራእይ ወሰደኝ።


በዚህ ጊዜ የእስራኤል አምላክ ክብር ከነበረበት ከኪሩብ በላይ ተነሥቶ ወደ ቤተ መቅደሱ መድረክ ሄደ። እግዚአብሔርም በፍታ የለበሰውን በጐኑም የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር ያነገበውን ሰው ጠራ፤


跟着我们:

广告


广告