Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 10:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 መንኰራኵሮቹ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜም ኪሩቤል ወደ ዞሩበት ወደ አራቱ አቅጣጫ ሁሉ መሄድ ይችሉ ነበር፤ ኪሩቤል በሚሄዱበት ጊዜ መንኰራኵሮቹ ወዲያ ወዲህ አይሉም ነበር፤ ኪሩቤል በሚሄዱበት ጊዜ ወዲያ ወዲህ ሳይሉ፣ ራስ ወደ ዞረበት ወደ ማንኛውም አቅጣጫ ይጓዙ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሲሄዱም በአራቱም ጎናቸው ይሄዱ ነበር፥ ሲሄዱም አይዞሩም ነበር፥ ራስ ወደዞረበት ስፍራ ወደዚያ ይከተሉ ነበር፥ ሲሄዱም አይዞሩም ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ወደ ፊታቸው በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ወደ የትኛውም አቅጣጫ ሳይዞሩ በቀጥታ ይሄዳሉ፤ የፊቱ መንኰራኲር ወደ የትኛውም አቅጣጫ ቢሄድ ሌሎቹ ሳይዞሩ በቀጥታ ይከተላሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሲሔ​ዱም በአ​ራቱ ጎድ​ና​ቸው ይሄዱ ነበር። ሲሄ​ዱም ወዲ​ያና ወዲህ አይ​ሉም ነበር፤ መጀ​መ​ሪ​ያው ወደ​ሚ​ያ​መ​ለ​ክ​ት​በት ስፍራ ይሄዱ ነበር፤ ሲሄ​ዱም ወዲ​ያና ወዲህ አይ​ሉም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሲሄዱም በአራቱ ጐድናቸው ይሄዱ ነበር፥ ሲሄዱም አይገላመጡም ነበር፥ ራሱ ወደምታመለክትበት ስፍራ ወደዚያ ይከተሉ ነበር፥ ሲሄዱም አይገላመጡም ነበር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 10:11
6 交叉引用  

በሚሄዱበት ጊዜም፣ ፍጡራኑ ወደሚዞሩበት ወደ አራቱ አቅጣጫ ሁሉ መንቀሳቀስ ይችሉ ነበር፤ ፍጡራኑ በሚሄዱበትም ጊዜ መንኰራኵሮቹ ወዲያና ወዲህ አይሉም ነበር።


መንፈስ ወደሚሄድበት ሁሉ ይሄዳሉ፤ የሕያዋኑ ፍጡራን መንፈስ በውስጣቸው ስላለ መንኰራኵሮቹ ዐብረዋቸው ይነሣሉ፤


በአራቱ ጐኖቻቸው ባሉት ክንፎቻቸው ሥር የሰው እጅ ነበራቸው። አራቱም ፊቶችና ክንፎች ነበሯቸው፤


የአራቱም መልክ ይመሳሰል ነበር፤ እያንዳንዱም መንኰራኵር በመንኰራኵር ውስጥ ተሰክቶ የተሠራ ይመስል ነበር።


ፊታቸውም በኮቦር ወንዝ አጠገብ ካየኋቸው ጋራ ይመሳሰል ነበር፤ እያንዳንዱም ቀጥ ብሎ ወደ ፊት ይሄድ ነበር።


跟着我们:

广告


广告