ሕዝቅኤል 1:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 የመንኰራኵሮቹ መልክና አሠራር እንዲህ ነበር፤ እንደ ቢረሌ ያንጸባርቁ ነበር፤ የአራቱም ቅርጽ ተመሳሳይ ሆኖ፤ እያንዳንዱ መንኰራኵር በመንኰራኵር ውስጥ ተሰክቶ የተሠራ ይመስል ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 የመንኰራኵሩም መልክና አሠራር የቢረሌ መልክ ይመስል ነበር፥ የአራቱም መልክ አንድ ዓይነት ነበር፥ መልካቸውና አሠራራቸው በመንኰራኵር መካከል ያለ መንኰራኵር ይመስል ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 አራቱም መንኰራኲሮች ተመሳሳይ ነበሩ፤ እያንዳንዱም እንደ ከበረ ዕንቊ ያንጸባርቅ ነበር፤ እንዲሁም እያንዳንዱ አንዱ መንኰራኲር በሌላው መንኰራኲር ውስጥ የሚተላለፍ ይመስል ነበር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 የመንኰራኵሩም መልክ እንደ ቢረሌ ነበረ፤ አራቱም አንድ አምሳያ ነበሩ፤ ሥራቸውም በመንኰራኵር ውስጥ እንዳለ መንኰራኵር ነበረ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 የመንኰራኵሩም መልክ እንደ ቢረሌ ነበረ፥ አራቱም አንድ አምሳያ ነበሩ፥ ሥራቸውም በመንኰራኵር ውስጥ እንዳለ መንኰራኵር ነበረ። 参见章节 |