Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 1:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የሕያዋን ፍጡራኑ መልክም እንደሚነድ የከሰል ፍምና የተቀጣጠለ ችቦ ይመስል ነበር፤ በፍጡራኑ መካከል እሳት ወዲያ ወዲህ ይንቀሳቀስ ነበር፤ ብርሃኑም ደማቅ ነበር፤ ከእሳቱም ውስጥ መብረቅ ይወጣ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የሕያዋኑም መልክ የሚነድድ የእሳት ፍም ይመስል ነበር፥ በሕያዋኑም መካከል የሚነድድ ችቦ የሚመስል ወዲህና ወዲያ ይዘዋወር ነበር፥ እሳቱም ብርሃን ነበረው፥ ከእሳቱም መብረቅ ይወጣ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በሕያዋን ፍጥረቶቹ መካከል እንደሚነድ ከሰል እሳት የሚመስል ነገር ነበር፤ እርሱም በፍጥረቶቹ መካከል ወዲያና ወዲህ የሚንቀሳቀስ ችቦ ይመስል ነበር፤ እሳቱ ብሩህ ነበር፤ መብረቅም ከዚያ ይወጣ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በእ​ን​ስ​ሶ​ቹም መካ​ከል እን​ደ​ሚ​ነ​ድድ የእ​ሳት ፍም ያለ አም​ሳያ ነበረ፤ በእ​ን​ስ​ሶቹ መካ​ከል ወዲ​ህና ወዲያ የሚ​ሄድ እንደ ፋና ያለ አም​ሳያ ነበረ፤ ለእ​ሳ​ቱም ፀዳል ነበ​ረው፤ ከእ​ሳ​ቱም መብ​ረቅ ይወጣ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በእንስሶቹ መካከል እንደሚነድድ የእሳት ፍም ያለ ምስያ ነበረ፥ በእንስሶች መካከል ወዲህና ወዲያ የሚሄድ እንደ ፋና ያለ ምስያ ነበረ፥ ለእሳቱም ፀዳል ነበረው፥ ከእሳቱም መብረቅ ይወጣ ነበር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 1:13
11 交叉引用  

ፀሓይ ገብታ ከጨለመ በኋላ የምድጃ ጢስና የሚንበለበል ፋና ታየ፤ በተከፈለውም ሥጋ መካከል ዐለፈ።


መላእክትህን መንፈስ፣ አገልጋዮችህንም የእሳት ነበልባል ታደርጋለህ።


እግራቸው ቀጥ ያለ ነበር፤ ኰቴያቸውም እንደ ጥጃ ኰቴ ያለ ሲሆን፣ እንደ ተወለወለ ናስም ያብለጨልጭ ነበር።


እግዚአብሔርም በፍታ የለበሰውን ሰው፣ “በኪሩቤል ሥር ወዳሉት መንኰራኵሮች መካከል ግባ፤ በኪሩቤል መካከል ካለውም የእሳት ፍም እጅህን ሞልተህ ዝገን፤ በከተማዪቱም ላይ በትነው” አለው። ሰውየውም እያየሁት ገባ።


“እኔም ስመለከት፣ “ዙፋኖች ተዘረጉ፤ ጥንታዌ ጥንቱም ተቀመጠ፤ ልብሱ እንደ በረዶ ነጭ ነበረ፤ የራሱም ጠጕር እንደ ጥጥ ነጭ ነበረ፤ ዙፋኑ የእሳት ነበልባል፣ መንኰራኵሮቹም ሁሉ እንደሚነድድ እሳት ነበሩ።


መልኩ እንደ መብረቅ ብሩህ፣ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበር።


መከራን ለተቀበላችሁት ለእናንተም ሆነ ለእኛ ደግሞ ዕረፍት ይሰጠናል። ይህም የሚሆነው ጌታ ኢየሱስ በሚንበለበል እሳት ከኀያላን መላእክት ጋራ ከሰማይ በሚገለጥበት ጊዜ ነው።


ከዚህ በኋላ ሌላ ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ እርሱም በራሱ ላይ ቀስተ ደመና ነበር። ፊቱ እንደ ፀሓይ፣ እግሮቹ እንደ እሳት ዐምዶች ነበሩ።


ከዚህ በኋላ ታላቅ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ ከክብሩም ነጸብራቅ የተነሣ ምድር በራች፤


ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ፣ ነጐድጓድም ወጣ፤ በዙፋኑ ፊት ሰባት መብራቶች ይበሩ ነበር፤ እነዚህም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።


跟着我们:

广告


广告