Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 8:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ሙሴም እንዲህ አለ፤ “ከአንተ እንደ ተለየሁ ወዲያውኑ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ነገም ዝንቡ ሁሉ ከፈርዖን፣ ከሹማምቱና ከሕዝቡ ይወገዳል። ብቻ ሕዝቡ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዲሠዉ ባለመፍቀድ ከዚህ ቀደም ፈርዖን አታልሎ እንዳደረገው አሁንም እንዳያደርግ ርግጠኛ ይሁን።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “በነገው ቀን ዝንቦቹ ከአንተና ከመኳንንቱ ከሕዝቡም ዘንድ እንዲወገዱ ከአንተ እንደ ተለየሁ አሁኑኑ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ነገር ግን ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ይሠዉ ዘንድ እንዳይሄዱ በመከልከል እንደገና ልታሞኘኝ አይገባም።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ሙሴም፥ “እነሆ፥ ከአ​ንተ ዘንድ እወ​ጣ​ለሁ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጸ​ል​ያ​ለሁ፤ የውሻ ዝን​ቡም ከአ​ንተ፥ ከሹ​ሞ​ች​ህና ከሕ​ዝ​ብህ ነገ ይር​ቃል፤ ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠዉ ዘንድ ሕዝ​ቡን እን​ደ​ማ​ት​ለ​ቅቅ እን​ደ​ገና ማታ​ለ​ልን አት​ድ​ገም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ሙሴም፥ “እነሆ ከአንተ ዘንድ እወጣለሁ፤ የዝንቡም መንጎች ከፈርዖን፥ ከባሪያዎቹም፥ ከሕዝቡም ነገ እንዲሄዱ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ይሠዋ ዘንድ ሕዝቡን እንዳይለቅቅ ፈርዖን እንደገና አያታልለን” አለ።

参见章节 复制




ዘፀአት 8:29
9 交叉引用  

እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፤ “ሥራህ እንዴት ግሩም ነው! ጠላቶችህ ከኀይልህ ታላቅነት የተነሣ፣ በፊትህ ይርዳሉ።


ፈርዖን ችግሩ ጋብ ማለቱን ባየ ጊዜ ግን ልክ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ልቡን በማደንደን ሙሴንና አሮንን አልሰማቸውም።


ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ጓጕንቸሮቹን ከእኔና ከሕዝቤ ያርቅ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ፤ ከዚያም ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን ትሠዉ ዘንድ ሕዝቡ እንዲሄዱ እፈቅዳለሁ”።


ሆኖም አንተና ሹማምትህ አሁንም ቢሆን እግዚአብሔር አምላክን እንደማትፈሩ ዐውቃለሁ።”


ነቢዩ ኤርምያስም፣ “ሰምቻችኋለሁ፤ እንዳላችሁት ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር በርግጥ እጸልያለሁ፤ እግዚአብሔር ያለኝን ሁሉ አንዳች ሳላስቀር እነግራችኋለሁ” አላቸው።


አትታለሉ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳል።


跟着我们:

广告


广告