Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 6:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሙሴ ግን እግዚአብሔርን፣ “እስራኤላውያን ያልሰሙኝ፣ ፈርዖን እንዴት ይሰማኛል፤ እኔ ለራሴ ተብታባ ሰው ነኝ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሙሴም በጌታ ፊት፦ “እነሆ የእስራኤል ልጆች አልሰሙኝም፤ ታድያ እንዴት ፈርዖን ይሰማኛል? እኔ ደግሞ ከንፈሬ ያልተገረዘ ሰው ነኝ” ብሎ ተናገረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ነገር ግን ሙሴ “ወገኖቼ እስራኤላውያን እንኳ አልሰሙኝም፤ ታዲያ፥ ንጉሡ እንዴት ሊሰማኝ ይችላል? እንደምታየኝ እኔ ኰልታፋ ነኝ” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት፥ “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አል​ሰ​ሙ​ኝም፤ እን​ዴ​ትስ ፈር​ዖን ይሰ​ማ​ኛል? እኔም አን​ደ​በተ ርቱዕ አይ​ደ​ለ​ሁም” ብሎ ተና​ገረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሙሴም በእግዚአብሔር ፊት፥ “እነሆ የእስራኤል ልጆች አልሰሙኝም፤ እንዴትስ ፈርዖን ይሰማኛል? ይልቁንም እኔ ከንፈረ ቈላፍ ነኝ” ብሎ ተናገረ።

参见章节 复制




ዘፀአት 6:12
16 交叉引用  

ሙሴ እግዚአብሔርን፣ “ወደ ፈርዖን የምሄድና የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ የማወጣ እኔ ማን ነኝ?” አለው።


ሙሴም እግዚአብሔርን፣ “ወደ እስራኤል ልጆች ሄጄ፣ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል’ ስላቸው ‘ስሙ ማን ነው?’ ብለው ቢጠይቁኝ ምን እላቸዋለሁ?” አለው።


ሙሴም “ባያምኑኝስ፤ ቃሌን ባይቀበሉስ፤ ‘እግዚአብሔር አልተገለጠልህም’ ቢሉኝስ?” ብሎ መለሰ።


ሙሴም እግዚአብሔርን፣ “ጌታ ሆይ፤ ቀድሞም ሆነ፣ አንተ ከባሪያህ ጋራ ከተነጋገርህ ወዲህ፣ ከቶ አንደበተ ርቱዕ ሰው አይደለሁም። እኔ ኰልታፋና ንግግር የማልችል ሰው ነኝ” አለው።


በዚህ ሁኔታ እግዚአብሔር ስለ እስራኤላውያንና ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ለሙሴና ለአሮን ነገራቸው፤ እስራኤላውያንንም ከግብጽ እንዲያወጡ አዘዛቸው።


ሙሴ ግን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “ፈርዖን ምን ብሎ ይሰማኛል? አንደበቴ ኰልታፋ ነው።”


ሙሴ ይህን ለእስራኤላውያን ነገራቸው፤ ተስፋ ከመቍረጣቸውና ከአስከፊ እስራታቸው የተነሣ ግን አላደመጡትም።


እኔም፣ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይተዋልና ጠፍቻለሁ፣ ወዮልኝ!” አልሁ።


እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዴት እንደምናገር አላውቅም፤ ገና ሕፃን ልጅ ነኝና” አልሁ።


ለማን ልናገር? ማንን ላስጠንቅቅ? ማንስ ይሰማኛል? እነሆ፣ ጆሮዎቻቸው አልተገረዙምና፣ መስማት አይችሉም። በእግዚአብሔር ቃል ይሣለቃሉ፤ ደስም አይሰኙበትም።


እነርሱም ግብጽ፣ ይሁዳ፣ ኤዶም፣ አሞን፣ ሞዓብና ጠጕራቸው ዙሪያውን የሚከረከም የበረሓ ነዋሪዎች ሁሉ ናቸው፤ እነዚህ ሕዝቦች ሁሉ በርግጥ የተገረዙ አይደሉምና፤ የእስራኤልም ቤት ሁሉ ልባቸው አልተገረዘም።”


ይኸውም፣ እኔ ጠላት እንድሆንባቸውና ወደ ጠላቶቻቸው ምድር እንድሰድዳቸው ያደረገኝን ኀጢአት ቢናዘዙ፣ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድና ስለ ኀጢአታቸው የሚገባውን ቅጣት ቢቀበሉ፣


“እናንተ ልባችሁና ጆሯችሁ ያልተገረዘ! ዐንገተ ደንዳኖች ልክ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ሁልጊዜ ትቃወማላችሁ።


አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ እንድትወድደው፣ በሕይወትም እንድትኖር፣ አምላክህ እግዚአብሔር የአንተንና የዘርህን ልብ ይገርዛል።


跟着我们:

广告


广告