ዘፀአት 5:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም21 “እግዚአብሔር ይይላችሁ፤ ይፍረድባችሁም፤ ፈርዖንና ሹማምቱ እንዲጠየፉን አደረጋችሁ፤ እንዲገድሉን በእጃቸው ሰይፍ ሰጣችኋቸው” አሏቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 እነርሱም፦ “ጌታ እናንተ ላይ ይፍረድባችሁ፥ ሽታችንን በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት አግምታችሁታልና፥ እንዲገድሉንም ሰይፍን በእጃቸው አስቀምጣችኋዋልና” አሉአቸው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ሙሴንና አሮንንም “በንጉሡ በፈርዖንና በመኳንንቱ ዘንድ እጅግ እንድንጠላ በማድረጋችሁና በሰይፍ ይገድሉንም ዘንድ ምክንያት በመሆናችሁ፥ እግዚአብሔር ይይላችሁ፤ እርሱም ይፍረድባችሁ፤” አሉአቸው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 እነርሱም፥ “በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት ሽታችንን አግምታችሁታልና፥ ይገድለንም ዘንድ ሰይፍን በእጁ ሰጥታችሁታልና እግዚአብሔር ይመልከታችሁ፤ ይፍረድባችሁም” አሉአቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 እነርሱም፦ “በፈርዖንና በባሪያዎቹ ፊት ሽታችንን አግምታችሁታልና፥ ይገድሉንም ዘንድ ሰይፍን በእጃቸው ሰጥታችኋቸዋልና እግዚአብሔር ይመልከታችሁ፤ ይፍረድባችሁም፤” አሉአቸው። 参见章节 |