Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 39:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው በኤፉዱ የትከሻ ንጣዮች ላይ ለእስራኤል ልጆች እንደ መታሰቢያ ድንጋዮች አያያዟቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ለእስራኤል ልጆች የመታሰቢያ ድንጋዮች እንዲሆኑ በኤፉዱ በትከሻው ላይ አደረጋቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እነርሱም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ነገድ በመወከል እንዲታሰቡ በትከሻ ላይ በሚወርዱት በኤፉዱ ጥብጣቦች ላይ አኖሩአቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የመ​ታ​ሰ​ቢያ ድን​ጋ​ዮች ይሆኑ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው፥ በል​ብሰ መት​ከፉ ጫን​ቃ​ዎች ላይ አደ​ረ​ጓ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ለእስራኤል ልጆች የመታሰቢያ ድንጋዮች ይሆኑ ዘንድ በኤፉዱ ጫንቃዎች ላይ አደረጋቸው።

参见章节 复制




ዘፀአት 39:7
7 交叉引用  

እኔም፣ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፤ እኛ ባሪያዎቹ እንደ ገና ሥራውን እንጀምራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ድርሻ ወይም ይገባናል የምትሉት ወይም የታሪክ መታሰቢያ የላችሁም” ስል መለስሁላቸው።


ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ ድንጋዮች ይሆኑ ዘንድ በኤፉዱ ትከሻ ላይ ካሉት ንጣዮች ጋራ አያይዛቸው፤ በእግዚአብሔር ፊት መታሰቢያ እንዲሆኑ አሮን ስሞቹን በትከሻው ላይ ይሸከማቸው።


“አሮን ወደ መቅደሱ በሚገባበት ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ለዘላለም መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በፍርድ መስጫው ደረት ኪስ በልቡ ላይ ይሸከም።


መተሳሰር እንዲችል ሆኖ፣ ዳርና ዳር ከሚገኙት ከሁለቱ ጐኖች ጋራ የተያያዙ ሁለት የትከሻ ንጣዮች ይኑሩት።


እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ወንጌል በሚሰበክበት በዓለም ዙሪያ ሁሉ፣ በማንኛውም ስፍራ እርሷ ያደረገችው መታሰቢያ ሆኖ ይነገርላታል።”


የዮርዳኖስ ወንዝ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት መቆሙን፣ እንዲሁም ታቦቱ ዮርዳኖስን በሚሻገርበት ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ ውሃ መቆሙን፣ እነዚህ ድንጋዮች ለእስራኤል ሕዝብ የዘላለም መታሰቢያ መሆናቸውን ንገሯቸው።”


跟着我们:

广告


广告