Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 39:43 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 ሙሴ ሥራውን አየ፤ ልክ እግዚአብሔር እንዳዘዘው መሥራታቸውንም ተመለከተ፤ ስለዚህ ባረካቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ሙሴም ሥራውን ሁሉ አየ፥ እነሆ ልክ ጌታ እንዳዘዘው አድርገውት ነበር፤ እንዲሁ አድርገውት ነበር፤ ሙሴም ባረካቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ሙሴም ሁሉን ነገር መርምሮ ልክ እግዚአብሔር ባለው መሠረት መሥራታቸውን አረጋገጠ፤ ስለዚህም ሙሴ ባረካቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 ሙሴም ሥራ​ውን ሁሉ አየ፤ እነ​ሆም፥ አድ​ር​ገ​ውት ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ አድ​ር​ገ​ውት ነበር፤ ሙሴም ባረ​ካ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ሙሴም ሥራውን ሁሉ አየ፥ እነሆም አድርገውት ነበር፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘው እንዲሁ አድርገውት ነበር፤ ሙሴም ባረካቸው።

参见章节 复制




ዘፀአት 39:43
24 交叉引用  

እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፤ እነሆም፣ እጅግ መልካም ነበረ። መሸ፤ ነጋም፤ ስድስተኛ ቀን።


አብራምንም እንዲህ ሲል ባረከው፤ “ሰማይንና ምድርን የፈጠረ ልዑል አምላክ አብራምን ይባርክ፤


ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረቱን መሥዋዕት ካቀረበ በኋላ ሕዝቡን በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም ባረከ።


በዐሥራ አንደኛው ዓመት ቡል በተባለውም በስምንተኛው ወር ቤተ መቅደሱ በዝርዝር ጥናቱ መሠረት እንደ ታቀደው ተፈጸመ፤ ሠርቶ የጨረሰውም በሰባት ዓመት ጊዜ ውስጥ ነበር።


መላው የእስራኤል ጉባኤ በዚያ ቆሞ ሳለ፣ ንጉሡ ፊቱን ወደ እነርሱ መልሶ ጉባኤውን ባረከ።


ከዚያም ቆሞ መላውን የእስራኤልን ጉባኤ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ ሲል መረቀ፤


ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረቱን መሥዋዕት ካቀረበ በኋላ፣ ሕዝቡን በእግዚአብሔር ስም ባረከ።


ከዚያም ካህናቱና ሌዋውያኑ ተነሥተው ሕዝቡን ባረኩ፤ እግዚአብሔርም ሰማቸው፤ ጸሎታቸውም ወደ ሰማይ ወደ ቅዱሱ ማደሪያው ደረሰ።


መላው የእስራኤል ጉባኤ በዚያ ቆሞ ሳለ፣ ንጉሡ ፊቱን ወደ እነርሱ መልሶ ጉባኤውን ባረከ።


ሕዝቡም በኢየሩሳሌም ለመኖር በራሳቸው ፈቃድ የተነሣሡትን ሰዎች ሁሉ አመሰገኑ።


የእግዚአብሔር ክብር ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤ እግዚአብሔር በሥራው ደስ ይበለው፤


ደግሞም አገልጋይህ በርሱ ጥንቃቄ ያደርጋል፤ እርሱንም መጠበቅ ወሮታ አለው።


እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዛቸው አደረጉ።


ማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ ልክ እኔ በማሳይህ ዕቅድ መሠረት ሥሩት።


እስራኤላውያን ልክ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሥራውን ሁሉ አከናወኑ።


ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን አለው፤


እግዚአብሔር እንዳዘዘውም መብራቶቹን በእግዚአብሔር ፊት አበራ።


ሙሴና አሮን እግዚአብሔር እንደ አዘዛቸው አደረጉ።


ስለዚህ እግዚአብሔር በነገረኝ መሠረት ወደ ኤፍራጥስ ሄጄ ሸሸግሁት።


“ይህ የዘላለም ሥርዐት ይሁናችሁ፤ በዚህም ሥርዐት መሠረት ለእስራኤላውያን ኀጢአት ሁሉ በዓመት አንድ ጊዜ ስርየት ይደረግ።” እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ ተደረገ።


ከዚያም ኢያሱ መርቆ አሰናበታቸው፤ እነርሱም ወደ ቤታቸው ተመለሱ።


ሙሴ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ በባሳን ምድር ርስት ሰጥቷቸው ነበር፤ ለቀረው እኩሌታ ደግሞ ኢያሱ ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ከወንድሞቻቸው ጋራ ርስት ሰጣቸው። ኢያሱ ወደ ቤታቸው እንዲገቡ ባሰናበታቸው ጊዜ መረቃቸው፤


跟着我们:

广告


广告