Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 34:35 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 የእስራኤልም ልጆች ፊቱ የሚያበራ መሆኑን አዩ፤ ከዚያም ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋራ ለመነጋገር ተመልሶ እስኪሄድ ድረስ መሸፈኛውን መልሶ በፊቱ ላይ ያደርግ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 የእስራኤል ልጆች የሙሴ ፊት እንዳንጸባረቀ ያዩ ነበር፤ ሙሴም ከእርሱ ጋር ለመነጋገር በፊቱ እስኪገባ ድረስ እንደገና በፊቱ ላይ መሸፈኛ ያደርግ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 እነርሱም ፊቱ ሲያበራ ያዩት ነበር፤ ስለዚህም ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ወደዚያ እስከሚሄድበት ጊዜ ድረስ ፊቱን በሻሽ ይሸፍን ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የሙ​ሴን ፊት እን​ዳ​ን​ጸ​ባ​ረቀ ያዩ ነበር፤ እር​ሱም ከእ​ርሱ ጋር ሊነ​ጋ​ገር እስ​ኪ​ገባ ድረስ እንደ ገና በፊቱ መሸ​ፈኛ ያደ​ርግ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 የእስራኤልም ልጆች የሙሴን ፊት ቁርበት እንዳንጸባረቀ ያዩ ነበር፤ እርሱም ከእርሱ ጋር ሊነጋገር እስኪገባ ድረስ እንደ ገና በፊቱ መሸፈኛ ያደርግ ነበር።

参见章节 复制




ዘፀአት 34:35
9 交叉引用  

ሙሴ የእስራኤልን ማኅበረ ሰብ ሁሉ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር እንድትፈጽሟቸው ያዘዛችሁ ነገሮች እነዚህ ናቸው፤


ነገሮችን መግለጽ የሚችል፣ እንደ ጠቢብ ያለ ሰው ማን ነው? ጥበብ የሰውን ፊት ታበራለች፤ የከበደ ገጽታውንም ትለውጣለች።


ጥበበኞች እንደ ሰማይ ጸዳል፣ ብዙዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ።


በዚያ ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሓይ ያበራሉ። ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ።


እንደዚሁም ሰዎች መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማይ ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ በሰዎች ፊት ይብራ።


ዮሐንስ እየነደደ ብርሃን የሚሰጥ መብራት ነበረ፤ እናንተም ለጥቂት ጊዜ በብርሃኑ ደስ ልትሠኙ ወደዳችሁ።


እስራኤላውያን የፊቱ ማንጸባረቅ እየጠፋ ሲሄድ መጨረሻውን እንዳይመለከቱ፣ ፊቱን በጨርቅ እንደ ሸፈነው እንደ ሙሴ አይደለንም።


ይኸውም በጠማማና በክፉ ትውልድ መካከል ንጹሓንና ያለ ነቀፋ፣ ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች ሆናችሁ፣ እንደ ከዋክብት በዓለም ሁሉ ታበሩ ዘንድ ነው።


跟着我们:

广告


广告