ዘፀአት 34:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 “የመንጋህ ወይም የበግና የፍየልህ፣ የቀንድ ከብትህ ተባዕት በኵር ሁሉ ሳይቀር፣ ከማሕፀን በኵር ሆኖ የሚወጣ ሁሉ የእኔ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ማኅፀንን የሚከፍት ሁሉ የእኔ ነው፤ የከብትህም ተባዕት ሁሉ፥ የበሬህም፥ የበግህም በኩር የእኔ ነው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 “በኲር ሆኖ የሚወለድ ወንድ ልጅ ሁሉ የእኔ ነው፤ የማንኛውም እንስሳ ተባዕት ሁሉ በሬም ሆነ በግ የእኔ ነው፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 መጀመሪያ የሚወለድ ተባት ሁሉ የእኔ ነው፤ የላምህም በኵር፥ የበግህም በኵር፥ የበሬህም በኵር ሁሉ የእኔ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ማኅፀንንም የሚከፍት ሁሉ የእኔ ነው፤ የከብትህም ተባት በኵር ሁሉ፥ በሬም ቢሆን በግም ቢሆን፥ የእኔ ነው። 参见章节 |