Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 33:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እግዚአብሔርም ሙሴን፣ “እስራኤላውያንን፣ ‘እናንተ ዐንገተ ደንዳና ሕዝብ ናችሁ፤ ለአንዳፍታ እንኳ ከእናንተ ጋራ ዐብሬአችሁ ብሄድ አጠፋችሁ ነበር፤ አሁንም ጌጣጌጦቻችሁን አውልቁ፤ እናንተን ምን ማድረግ እንዳለብኝ እወስናለሁ’ ብለህ ንገራቸው” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጌታም ሙሴን፦ “ለእስራኤል ልጆች ‘እናንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ናችሁ፥ አንድ ጊዜ ከእናንተ ጋር ብወጣ አጠፋችኋለሁ፤ አሁንም በእናንተ ላይ የማደርገውን እንዳውቅ ጌጣችሁን አውጡ’ በላቸው አለው።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔርም ለሕዝቡ እንዲህ ብሎ እንዲነግረው ሙሴን አዞት ነበር፦ “እናንተ እልኸኞች ስለ ሆናችሁ ለአንድ አፍታ እንኳ አብሬአችሁ ብሄድ ፈጽሞ እደመስሳችኋለሁ፤ አሁንም ጌጣጌጦቻችሁን አስወግዱ፤ ስለ እናንተ የማደርገውንም እወስናለሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እና​ንተ አን​ገተ ደን​ዳና ሕዝብ ናችሁ፤ ሌላ መቅ​ሠ​ፍት እን​ዳ​ላ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁና እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ፤ አሁ​ንም የክ​ብር ልብ​ሳ​ች​ሁ​ንና ጌጣ​ች​ሁን ከእ​ና​ንተ አውጡ፤ የማ​ደ​ር​ግ​ባ​ች​ሁ​ንም አሳ​ያ​ች​ኋ​ለሁ በላ​ቸው” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ለእስራኤል ልጆች፦ እናንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ናችሁ፥ አንድ ጊዜ በእናንተ መካከል ብወጣ አጠፋችኋለሁ፤ አሁንም የማደርግባችሁን አውቅ ዘንድ ጌጣችሁን ከእናንተ አውጡ በላቸው አለው።

参见章节 复制




ዘፀአት 33:5
16 交叉引用  

አድራጎታቸው እኔ ዘንድ እንደ ደረሰው ጩኸት መሆኑን ለማየት ወደዚያው እወርዳለሁ፤ እንደዚያ ካልሆነም ዐውቃለሁ።”


እርሱም፣ “እጅህን በብላቴናው ላይ አታሳርፍ፤ ምንም ጕዳት አታድርስበት፤ እነሆ፤ እግዚአብሔርን እንደምትፈራ ተረድቻለሁ፤ ልጅህን፣ ያውም አንዱን ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሣሣህምና” አለው።


እነርሱም እኩለ ሌሊት ላይ በድንገት ይሞታሉ፤ ሕዝብ ተንቀጥቅጦ ሕይወቱ ያልፋል፤ ኀያላኑም የሰው እጅ ሳይነካቸው ይወገዳሉ።


እግዚአብሔር ሆይ፤ መርምረኝ፤ ልቤንም ዕወቅ፤ ፈትነኝ፤ ሐሳቤንም ዕወቅ፤


እንዴት ፈጥነው በቅጽበት ጠፉ! በድንጋጤ ፈጽመው ወደሙ።


እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እነዚህን ሕዝብ አይቻቸዋለሁ፤ ዐንገተ ደንዳናዎችም ናቸው።


ስለዚህ እስራኤላውያን በኮሬብ ተራራ ላይ ጌጣጌጦቻቸውን አወለቁ።


በዚያ ቀን ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንድታለቅሱና በዋይታ እንድትጮኹ፣ ጠጕራችሁን እንድትነጩ ማቅም እንድትለብሱ ጠራችሁ።


የቱን ያህል እልኸኛ እንደ ነበርህ ዐውቃለሁና፤ የዐንገትህ ጅማት ብረት፣ ግንባርህም ናስ ነበር።


በሕዝቤ ላይ የደረሰው ቅጣት፣ የማንም እጅ ሳይረዳት፣ በድንገት ከተገለበጠችው፣ ሰዶም ላይ ከደረሰው ቅጣት ይልቅ ታላቅ ነው።


“አሁንም ቢሆን፣ በጾም፣ በልቅሶና በሐዘን፣ በፍጹም ልባችሁ ወደ እኔ ተመለሱ” ይላል እግዚአብሔር።


“ሁሉንም በአንድ ጊዜ እንዳጠፋቸው እናንተ ከዚህ ማኅበር ተለዩ።”


“እናንተ ልባችሁና ጆሯችሁ ያልተገረዘ! ዐንገተ ደንዳኖች ልክ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ሁልጊዜ ትቃወማላችሁ።


አምላክህ እግዚአብሔር ትእዛዞቹን መጠበቅህንና በልብህ ያለውን ለማወቅ፣ ትሑት ሊያደርግህና ሊፈትንህ በእነዚህ አርባ ዓመታት በዚህ ምድረ በዳ ጕዞህ ሁሉ እንዴት እንደ መራህ አስታውስ።


跟着我们:

广告


广告