Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 31:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ለሙሴ መናገሩን ከፈጸመ በኋላ፣ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላት፣ ሁለቱን የምስክር ጽላት ለርሱ ሰጠው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በሲና ተራራ ከሙሴ ጋር ንግግሩን ከፈጸመ በኋላ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላቶች የሆኑ ሁለት የምስክር ጽላቶችን ሰጠው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ማነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ በእግዚአብሔር ጣት በድንጋይ ላይ የተጻፈባቸውን ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶች ሰጠው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር በሲና ተራራ የተ​ና​ገ​ረ​ውን በፈ​ጸመ ጊዜ ሁለ​ቱን የም​ስ​ክር ጽላት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት የተ​ጻ​ፈ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እግዚአብሔርም ከሙሴ ጋር በሲና ተራራ የተናገረውን በፈጸመ ጊዜ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን ከድንጋይ የሆኑ ሁለቱን የምስክር ጽላቶች ሰጠው።

参见章节 复制




ዘፀአት 31:18
17 交叉引用  

ዮዳሄም የንጉሡን ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነለት፤ ኪዳኑንም ሰጠው፤ መንገሡን ዐወጁ፤ ቀብተውም አነገሡት። ከዚያም ሕዝቡ፣ “ንጉሡ ሺሕ ዓመት ይንገሥ” እያሉ በማጨብጨብ ደስታቸውን ከፍ ባለ ድምፅ ገለጹ።


እግዚአብሔር ሙሴን፣ “በተራራው ላይ ወደ እኔ ና፤ በዚህም ቈይ፤ እኔም መመሪያ እንዲሆናቸው ሕግና ትእዛዞች የጻፍሁባቸውን የድንጋይ ጽላት እሰጥሃለሁ” አለው።


ከዚያም ሙሴ ወደ ተራራው ሲወጣ ደመናው ውስጥ ገባ፤ በተራራውም ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቈየ።


አስማተኞቹም ፈርዖንን፣ “ይህ የእግዚአብሔር ጣት ነው” አሉት፤ ነገር ግን የፈርዖን ልብ ደንድኖ ስለ ነበር፣ ልክ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው አልሰማቸው አለ።


“ነገር ግን ከዚያ ጊዜ በኋላ፣ ከእስራኤል ቤት ጋራ የምገባው ኪዳን ይህ ነው” ይላል እግዚአብሔር፤ “ሕጌን በአእምሯቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ። እኔ አምላክ እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።


እኔ ግን አጋንንትን የማስወጣው በእግዚአብሔር መንፈስ ከሆነ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ መጥታለች።


እኔ ግን አጋንንትን የማወጣው በእግዚአብሔር ጣት ከሆነ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ እንደ መጣች ዕወቁ።


እናንተ በቀለም ሳይሆን በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ፣ በድንጋይ ጽላት ላይ ሳይሆን በሰው ልብ ጽላት ላይ የተጻፋችሁና በእኛ የተገለገላችሁ የክርስቶስ ግልጽ ደብዳቤ ናችሁ።


እግዚአብሔር በስብሰባው ቀን፣ በእሳት ውስጥ ሆኖ ለእናንተ የተናገራቸውንና ቀድሞ ጽፏቸው የነበሩትን ዐሥሩን ትእዛዞች በእነዚህ ጽላት ላይ ጻፋቸው። እግዚአብሔርም እነርሱን ለእኔ ሰጠኝ።


እርሱ ኪዳኑን ይኸውም እንድትከተሏቸው ያዘዛችሁን ዐሥርቱን ትእዛዛት ዐወጀላችሁ፤ ከዚያም በሁለት የድንጋይ ጽላት ላይ ጻፋቸው፤


እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳቱ፣ በደመናውና በድቅድቁ ጨለማ ውስጥ ለማኅበራችሁ ሁሉ በከፍተኛ ድምፅ የተናገራችሁ ትእዛዞቹ እነዚህ ናቸው፤ የጨመረውም ሌላ የለም፤ ትእዛዞቹንም በሁለት የድንጋይ ጽላት ላይ ጽፎ ሰጠኝ።


በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንትና በወርቅ የተለበጠው የኪዳኑ ታቦት ነበሩ፤ ይህም ታቦት መና ያለበትን የወርቅ መሶብ፣ የለመለመችውን የአሮንን በትርና ኪዳኑ የተጻፈበትን ጽላት ይዟል።


跟着我们:

广告


广告