ዘፀአት 29:40 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም40 ከመጀመሪያው የበግ ጠቦት ጋራ የኢፍ መስፈሪያ አንድ ዐሥረኛ ምርጥ ዱቄትን ተወቅጦ ከተጠለለ ሩብ ኢፍ ዘይት ጋራ ለውስና ሩብ ሂን ወይንን ደግሞ የመጠጥ መሥዋዕት በማድረግ አቅርብ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)40 ከአንዱ ጠቦት ጋር አሥረኛ እጅ የኢፍ መስፈሪያ መልካም ዱቄት ከአራተኛ እጅ የኢን መስፈሪያ ተወቅጦ ከተጠለለ ዘይት ጋር የተለወሰ፥ ለመጠጥ ቁርባን የሚሆን ደግሞ አራተኛ እጅ የኢን መስፈሪያ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም40 ከመጀመሪያው ጠቦት ጋር አንድ ኪሎ ግራም ምርጥ የሆነ የስንዴ ዱቄት ከአንድ ሊትር ተጨምቆ የተጠለለ የወይራ ዘይት ጋር ለውሰህ አቅርብ፤ አንድ ሊትር የወይን ጠጅም መባ አድርገህ አፍስስበት። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)40 ከአንዱ ጠቦትም ጋር የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ ዐሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት፥ ደግሞ ለመጠጥ ቍርባን የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)40 ከአንዱ ጠቦትም ጋር የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት፥ ደግሞ ለመጠጥ ቍርባን የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ። 参见章节 |