Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 29:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከዚያም በሆድ ዕቃዎች ያለውን ስብ ሁሉ፣ የጕበቱን መሸፈኛና ሁለቱንም ኵላሊቶች በዙሪያቸው ካለው ስብ ጋራ ወስደህ በመሠዊያው ላይ አቃጥላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ፥ በጉበቱ ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱን ኩላሊቶችና በላያቸው ያለውን ስብ ወስደህ በመሠዊያው ላይ ታቃጥላለህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከዚህ በኋላ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሞራ እንደ መረብ ሆኖ ጉበቱን የሚሸፍነውን ሞራ ሁለቱን ኲላሊቶቹንና እነርሱን የሚሸፍነውን ሞራ ወስደህ በመሠዊያው ላይ አቃጥለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ ሁሉ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ፥ ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በላ​ያ​ቸ​ውም ያለ​ውን ስብ ወስ​ደህ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ታስ​ቀ​ም​ጣ​ለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ በጉልበቱም ላይ ያለውን መረብ ሁለቱንም ኵላሊቶች በላያቸውም ያለውን ስብ ወስደህ በመሠዊያው ላይ ታቃጥላለህ።

参见章节 复制




ዘፀአት 29:13
29 交叉引用  

እንደ ውሃ ፈሰስሁ፤ ዐጥንቶቼም ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ፤ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፤ በውስጤም ቀለጠ።


ጥሬውን ሥጋ ወይም ቅቅሉን አትብሉ፤ ነገር ግን ጭንቅላቱን፣ እግሮቹንና ሆድ ዕቃውን በእሳት ላይ ጠብሳችሁ ብሉት።


ከዚያም አውራ በጉን በሙሉ በመሠዊያው ላይ አቃጥለው፤ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ጣፋጭ መዐዛና ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ነው።


“ከዚህ አውራ በግ ሥቡን፣ ላቱን፣ በሆድ ዕቃው ውስጥ ያለውን ስብ፣ የጕበቱን ሽፋን፣ ሁለቱን ኵላሊቶችና በዙሪያቸው ያለውን ሥብና ቀኙን ወርች ውሰድ፤ ይህ የክህነት አውራ በግ ነው።


ከዚያም ከእጃቸው ወስደህ ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋራ ለእግዚአብሔር መልካም መዐዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ አቃጥለው፤ ይህም ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።


“የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምኔ ነው?” ይላል እግዚአብሔር። “የሚቃጠለውን የአውራ በግና የሠቡ እንስሳትን ሥብ ጠግቤአለሁ፤ በበሬ፣ በበግ ጠቦትና በፍየል ደም ደስ አልሰኝም።


የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተነክራለች፤ ሥብ ጠግባለች፤ በበግ ጠቦትና በፍየል ደም፣ በአውራም በግ ኵላሊት ሥብ ተሸፍናለች። እግዚአብሔር በባሶራ ከተማ መሥዋዕት፣ በኤዶምም ታላቅ ዕርድ አዘጋጅቷልና።


መልካም መዐዛ ያለው ከሙን አልገዛህልኝም፤ በመሥዋዕትህ ሥብ አላጠገብኸኝም፤ ነገር ግን በኀጢአትህ አስቸገርኸኝ፤ በበደልህም አደከምኸኝ።


ካህኑም ወደ መሠዊያው ያምጣው፤ ራሱን ቈልምሞ ይቀንጥሰው፤ የተቈረጠውንም ራስ በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ደሙም በመሠዊያው አጠገብ ይንጠፍጠፍ፤


አቅራቢው የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን በውሃ ይጠብ፤ ካህኑም መባውን ሁሉ በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ይህም በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል።


የኀጢአት መሥዋዕቱንም በመሠዊያው ላይ ያቃጥል።


ካህኑም ደሙን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባለው በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይርጭ፤ ሥቡንም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሽታ እንዲሆን ያቃጥል።


የኅብረት መሥዋዕቱን እንዳቃጠለ ሁሉ ሥቡንም በሙሉ በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ በዚህም መሠረት ካህኑ የሰውየውን ኀጢአት ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል።


ሥቡን ከኅብረት መሥዋዕት በወጣበት አኳኋን ሥቡን ሁሉ ያውጣ፤ ካህኑም ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ በዚህም መሠረት ካህኑ የሰውየውን ኀጢአት ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል።


ሥቡ ከኅብረት መሥዋዕት ጠቦት በወጣበት አኳኋን ሥቡን ሁሉ ያውጣ፤ ካህኑም በመሠዊያው ላይ ለእግዚአብሔር በእሳት በሚቀርበው መሥዋዕት ላይ ያቃጥለው። በዚህ መሠረት ሰውየው የሠራውን ኀጢአት ካህኑ ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል።


በመሠዊያው ላይ ያለው እሳት ዘወትር ይንደድ፤ ምን ጊዜም አይጥፋ። ካህኑ ጧት ጧት እሳቱ ላይ ማገዶ ይጨምር፤ በእሳቱ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያዘጋጅ፤ በዚህም ላይ የኅብረት መሥዋዕቱን ሥብ ያቃጥል።


ሥቡን በሙሉ ያቅርብ፤ ይኸውም፦ ላቱን፣ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፣


ካህኑ ሥቡን በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ፍርምባው ግን ለአሮንና ለልጆቹ ይሰጥ።


ሁለቱን ኵላሊቶች፣ በኵላሊቶቹ ላይና በጐድኑ አጠገብ ያለውን ሥብ እንዲሁም የጉበቱን መሸፈኛ ከኵላሊቶቹ ጋራ አንድ ላይ አውጥቶ ያቅርብ።


ሙሴም የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ ሁሉ፣ የጕበቱን ሽፋን፣ ኵላሊቶችንና ሥባቸውን ወስዶ በመሠዊያው ላይ አቃጠለ።


ሥቡን፣ ላቱን፣ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ ሁሉ፣ የጕበቱን ሽፋን፣ ሁለቱን ኵላሊቶችና ሥባቸውን እንዲሁም ቀኝ ወርቹን ወሰደ፤


እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት የኀጢአት መሥዋዕቱን ሥብ፣ ኵላሊቶቹንና የጕበቱን ሽፋን በመሠዊያው ላይ አቃጠለው፤


የበሬውንና የአውራ በጉን ሥብ፦ ላቱን፣ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፤ ኵላሊቶቹንና የጕበቱን ሽፋን፣


“የተቀደሱ ስለ ሆኑ የበሬ፣ የበግ ወይም የፍየል በኵር የሆኑትን አትዋጃቸውም፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ ትረጨዋለህ፤ ሥባቸውንም ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ ታቃጥለዋለህ።


ሰውየውም፣ “በመጀመሪያ ሥቡ ይቃጠል፤ ከዚያ በኋላ የምትፈልገውን ትወስዳለህ” ቢለው እንኳ አገልጋዩ፣ “አይሆንም፤ አሁኑኑ ስጠኝ፤ አለዚያ በግድ እወስዳለሁ” ይለው ነበር።


跟着我们:

广告


广告