ዘፀአት 28:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 በጥበብ የተጠለፈው የወገብ መታጠቂያ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ሐር ከኤፉድ ጋራ አንድ ወጥ ሆኖ የተሠራ ይሁን። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 በላዩ ያለው በብልሃት የተጠለፈው የኤፉዱ መታጠቂያ ከእርሱ ጋር ወጥ ሆኖ ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ የተሠራ ይሁን። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ኤፉዱ ከተሠራባቸው ተመሳሳይ ነገሮች በብልኀት የተጠለፈ መታጠቂያ አንድ ላይ እንደ ተሠራ ሆኖ ከኤፉዱ ጋር ይጣበቅ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 በላዩም የተጠለፈው የልብሰ መትከፍ ቋድ እንደ እርሱ፥ ከእርሱም ጋር አንድ ይሁን፤ ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃም ከተፈተለ፥ ከጥሩ በፍታም የተሠራ ይሁን። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 በላዩም መታጠቂያ ሆኖ በብልሃት የተጠለፈው የኤፉድ ቍድ እንደ እርሱ ከእርሱም ጋር አንድ ይሁን፤ ከወርቅና ከሰማያዊ ከሐምራዊ ከቀይ ግምጃም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም የተሠራ ይሁን። 参见章节 |