Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 27:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ጥቅማቸው ምንም ዐይነት ይሁን፣ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በሙሉ የድንኳኑና የአደባባዩ ካስማዎችም ሁሉ ሳይቀሩ ከንሓስ የተሠሩ ይሁኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ለአገልግሎት ሁሉ የሚሆኑ የማደሪያው ዕቃ ሁሉ፥ ካስማዎቹ ሁሉ የአደባባዩም ካስማዎች ሁሉ፥ የነሐስ ይሁኑ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በድንኳኑ ውስጥ የሚገኙት ለማናቸውም ጥቅም የሚውሉ የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ፥ የድንኳኑና የአደባባዩ ካስማዎች ሁሉ ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ለማ​ገ​ል​ገል ሁሉ የድ​ን​ኳን ዕቃ ሁሉ፥ አው​ታ​ሮቹ ካስ​ማ​ዎ​ቹም ሁሉ፤ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ካስ​ማ​ዎች ሁሉ የናስ ይሁኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ለማገልገል ሁሉ የማደሪያው ዕቃ ሁሉ፥ ካስማዎቹም ሁሉ የአደባባዩም ካስማዎች ሁሉ፥ የናስ ይሁኑ።

参见章节 复制




ዘፀአት 27:19
14 交叉引用  

“አሁን ግን እግዚአብሔር አምላካችን ቅሬታ ይተውልን ዘንድ፣ በመቅደሱም ውስጥ ጽኑ ስፍራ ይሰጠን ዘንድ፣ ለጥቂት ጊዜ ቸርነቱን አሳይቶናል፤ ስለዚህ አምላካችን ለዐይናችን ብርሃን ሰጠን፤ በባርነትም ሳለን ለጥቂት ጊዜ ዕረፍት ሰጠን።


አደባባዩ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ፣ ስፋቱ ዐምሳ ክንድ ሆኖ፣ በቀጭኑ ከተፈተለ ማግ ቁመታቸው ዐምስት ክንድ የሆነ መጋረጃዎችና የንሓስም መቆሚያዎች ያሉት ይሁን።


“መብራቶቹ ያለማቋረጥ እንዲያበሩ ለመብራቱ የሚሆን ከወይራ ተጨምቆ የተጠለለ ንጹሕ ዘይት እንዲያመጡልህ እስራኤላውያንን እዘዛቸው።


ዕቃዎቹን ሁሉ ይኸውም የዐመድ ማስወገጃ ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፣ ሜንጦዎችንና የፍም መያዣዎችን ከንሓስ አብጃቸው።


ለመገናኛው ድንኳንና ለአደባባዩ የሚሆኑ የድንኳን ካስማዎችና ገመዶቻቸው፤


የማደሪያው ድንኳንና የአደባባዩ ዙሪያ ካስማዎች ሁሉ ከንሓስ የተሠሩ ነበሩ።


ለአደባባዩ ዙሪያ፣ ለመግቢያው እንዲሁም ለማደሪያው ድንኳን ካስማዎች ሁሉና ለአደባባዩ ዙሪያ ሁሉ እንዲሁ አገልግሎት ላይ አውለውት ነበር።


የአደባባዩ መጋረጃዎች ከምሰሶዎቹና ከመቆሚያዎቹ ጋራ፣ የአደባባዩ መግቢያ መጋረጃ፤ ገመዶቹና የአደባባዩ ድንኳን ካስማዎች፤ የማደሪያው የመገናኛው ድንኳን ዕቃዎች ሁሉ፤


የጠቢባን ቃላት እንደ ሹል የከብት መንጃ ናቸው፤ የተሰበሰቡ አባባሎቹም እጅግ ተቀብቅበው እንደ ገቡ ችንካሮች ሲሆኑ፣ ከአንድ እረኛ የተሰጡ ናቸው።


በዓላታችንን የምናከብርባትን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ ሰላማዊ መኖሪያ፣ የማትነቃነቅ ድንኳን የሆነችውን፣ ካስማዋ የማይነቀል፣ ከገመዷ አንዱ እንኳ የማይበጠሰውን፣ ኢየሩሳሌምን ዐይኖችህ ያያሉ።


ከይሁዳ፣ የማእዘን ድንጋይ፣ የድንኳን ካስማ፣ የጦርነት ቀስት፣ ገዥም ሁሉ ይወጣል።


እንዲሁም የአደባባዩን ዙሪያ ምሰሶዎች ከነመቆሚያ እግሮቻቸው፣ ከነካስማቸውና ከነገመዶቻቸው ይጠብቃሉ።


እንደዚሁም በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን ምሰሶዎች ከነመቆሚያ እግሮቻቸው፣ ካስማዎችን፣ ገመዶችን፣ ከእነዚሁ ጋራ ያሉትን ዕቃዎች ሁሉና ማንኛውም ለአገልግሎቱ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ ይሸከማሉ። እያንዳንዱ ሰው የሚሸከመውን ዕቃ ለይታችሁ በስሙ መድቡለት።


跟着我们:

广告


广告