Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 27:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 አደባባዩ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ፣ ስፋቱ ዐምሳ ክንድ ሆኖ፣ በቀጭኑ ከተፈተለ ማግ ቁመታቸው ዐምስት ክንድ የሆነ መጋረጃዎችና የንሓስም መቆሚያዎች ያሉት ይሁን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የአደባባዩ ርዝመት መቶ ክንድ፥ ስፋቱ አምሳ ክንድ ይሁን፥ ከፍታው አምስት ክንድ ይሁን፥ መጋረጃውም ከጥሩ በፍታ፥ እግሮቹም ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የድንኳኑ አደባባይ ርዝመቱ አርባ አራት ሜትር የጐኑ ስፋት ኻያ ሁለት ሜትር፥ ከፍታውም ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ይሁን፤ መጋረጃዎቹ ከጥሩ በፍታ የተሠሩ ሆነው የነሐስ እግሮች ይኑሩአቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የአ​ደ​ባ​ባዩ ርዝ​መት በየ​ገጹ መቶ ክንድ፥ ስፋ​ቱም በየ​ገጹ አምሳ ክንድ ይሁን፤ የመ​ጋ​ረ​ጃ​ውም ከፍታ አም​ስት ክንድ ይሁን፤ መጋ​ረ​ጃ​ውም ከጥሩ በፍታ፥ እግ​ሮ​ቹም ከናስ የተ​ሠሩ ይሁኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የአደባባዩ ርዝመት መቶ ክንድ ስፋቱም አምሳ ክንድ ይሁን፥ የመጋረጃውም ከፍታ አምስት ክንድ ይሁን፤ መጋረጃውም ከጥሩ በፍታ፥ እግሮቹም ከናስ የተሠሩ ይሁኑ።

参见章节 复制




ዘፀአት 27:18
3 交叉引用  

“በቀጭኑ ከተፈተለ የበፍታ ድርና በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ማግ በተሠሩ ዐሥር መጋረጃዎች ማደሪያ ድንኳኑን ሥራ፤ እጀ ብልኅ ሠራተኛም ኪሩቤልን ይጥለፍባቸው።


በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎች፣ ኵላቦችና የንሓስ መቆሚያዎች ይኑሯቸው።


ጥቅማቸው ምንም ዐይነት ይሁን፣ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በሙሉ የድንኳኑና የአደባባዩ ካስማዎችም ሁሉ ሳይቀሩ ከንሓስ የተሠሩ ይሁኑ።


跟着我们:

广告


广告