Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 26:33 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 መጋረጃውን በማያያዣዎቹ ላይ ስቀለው፤ የምስክሩንም ታቦት ከመጋረጃው በስተኋላ አስቀምጠው፤ መጋረጃውም መቅደሱን ከቅድስተ ቅዱሳኑ ይለያል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 መጋረጃውንም ከመያዣዎቹ በታች ታንጠለጥለዋለህ፥ በመጋረጃውም ውስጥ የምስክርን ታቦት አግባው፤ መጋረጃውም በቅድስቱና በቅድስተ ቅዱሳኑ መካከል መለያ ይሁናችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 መጋረጃውንም በድንኳኑ ጣራ ላይ በተርታ በተደረደሩት መያዣዎች ሥር ታንጠለጥለዋለህ፤ ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች የያዘውንም የቃል ኪዳን ታቦት ከመጋረጃው በስተኋላ በኩል ታኖረዋለህ፤ በዚህ ዐይነት መጋረጃው ቅድስት የተባለውን ስፍራ ከቅድስተ ቅዱሳኑ ይለያል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም በም​ሰ​ሶ​ዎች ላይ ስቀ​ለው፤ በመ​ጋ​ረ​ጃ​ውም ውስጥ የም​ስ​ክ​ሩን ታቦት አግ​ባው፤ መጋ​ረ​ጃ​ውም በቅ​ድ​ስ​ቱና በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ መካ​ከል መለያ ይሁ​ና​ችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 መጋረጃውንም ከመያዣዎቹ በታች ታንጠለጥለዋለህ፥ በመጋረጃውም ውስጥ የምስክርን ታቦት አግባው፤ መጋረጃውም በቅድስቱና በቅድስተ ቅዱሳኑ መካከል መለያ ይሁናችሁ።

参见章节 复制




ዘፀአት 26:33
16 交叉引用  

በቤተ መቅደሱም ውስጥ በስተኋላ በኩል፣ ሃያውን ክንድ ቅድስተ ቅዱሳን እንዲሆን፣ ከወለሉ አንሥቶ እስከ ጣራው ድረስ በዝግባ ሳንቃዎች ጋረደው፤


ካህናቱ ከቤተ መቅደሱ በወጡ ጊዜ፣ ደመና የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሞላው።


ከዚያም ካህናቱ የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት አምጥተው የቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ አግብተው ከኪሩቤል ክንፍ በታች ባለው ስፍራው አኖሩት።


እንደዚሁም ቅድስተ ቅዱሳኑን ሠራ፤ ርዝመቱ ከቤተ መቅደሱ ወርድ ጋራ እኩል ሲሆን፣ ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ስፋቱም ሃያ ክንድ ነበር፤ ውስጡንም በስድስት መቶ መክሊት የተጣራ ወርቅ ለበጠው።


የምሰጥህንም ምስክር በታቦቱ ውስጥ አኑር።


በወርቅ በተለበጡ ከግራር ዕንጨት በተሠሩና በአራቱ የብር መቆሚያዎች ላይ በቆሙት በአራቱ ምሰሶዎች፣ በወርቅ ኵላቦች ላይ አንጠልጥለው።


ሃያ ምሰሶዎች፣ ሃያ የንሓስ መቆሚያዎች፣ የብር ኵላቦችና በምሰሶዎቹም ላይ ዘንጎች ይኑሩት።


በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው በስተውጭ ይኸውም ከምስክሩ ታቦት ፊት ለፊት፣ አሮንና ወንድ ልጆቹ መብራቶቹን ከምሽት እስከ ንጋት በእግዚአብሔር ፊት እንዲበሩ ያድርጉ፤ ይህም በእስራኤላውያን ዘንድ ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ሥርዐት ይሆናል።


ለርሱም አራት ምሰሶዎች ከግራር ዕንጨት ሠርተው በወርቅ ለበጧቸው፤ ለእነርሱም አራት የወርቅ ኵላቦችንና አራት የብር መቆሚያዎችን አበጁላቸው።


ከዚያም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ታቦቱን ወደ ማደሪያው ድንኳን አስገብቶ መከለያ መጋረጃውን ሰቀለ፤ የምስክሩንም ታቦት ጋረደው።


የምስክሩን ታቦት በውስጡ አኑር፤ ታቦቱንም በመጋረጃው ጋርደው።


እርሱም የውስጠኛውን መቅደስ ርዝመት ለካ፤ ሃያ ክንድ ነበር፤ ወርዱም የውጪውን ግድግዳ ጨምሮ ሃያ ክንድ ነበር፤ እርሱም፣ “ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው” አለኝ።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመና ውስጥ እገለጣለሁና ወንድምህ አሮን በመጋረጃው ውስጥ ወዳለው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ማለት በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ፊት፣ በፈለገ ጊዜ ሁሉ እንዳይገባና እንዳይሞት ንገረው።


跟着我们:

广告


广告