Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 24:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ለእስራኤላውያን የእግዚአብሔር ክብር በተራራው ጫፍ ላይ እንደሚባላ እሳት ሆኖ ይታይ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በተራራው ራስ ላይ የጌታ ክብር ለእስራኤል ልጆች እንደሚባላ እሳት ሆኖ ታያቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በተራራው ጫፍ ላይ የተገለጠው የእግዚአብሔር ክብር በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ እንደሚባላ እሳት ይታይ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በተ​ራ​ራ​ውም ራስ ላይ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር መታ​የት እን​ደ​ሚ​ያ​ቃ​ጥል እሳት ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በተራራው ራስ ላይ በእስራኤል ልጆች ፊት የእግዚአብሔር ክብር መታየት እንደሚያቃጥል እሳት ነበረ።

参见章节 复制




ዘፀአት 24:17
14 交叉引用  

በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ፣ የመብረቅ ብልጭታ ወጣ።


ከአፍንጫው ጢስ ወጣ፤ ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤ ከውስጡም ፍሙ ጋለ።


በሦስተኛውም ቀን ይዘጋጁ፤ ምክንያቱም በዚያ ቀን በሕዝቡ ፊት እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ይወርዳል።


የሲና ተራራ እግዚአብሔር በእሳት ስለ ወረደበት በጢስ ተሸፍኖ ነበር። ጢሱ ከምድጃ እንደሚወጣ ጢስ ወደ ላይ ተትጐለጐለ፤ ተራራውም በሙሉ በኀይል ተናወጠ።


እዚያም የእግዚአብሔር መልአክ በቍጥቋጦው ውስጥ በሚንቀለቀል የእሳት ነበልባል መካከል ተገለጠለት። ሙሴም ቍጥቋጦው በእሳት ቢያያዝም እንኳ፣ አለመቃጠሉን አየ።


ወገቡ ከሚመስለው ጀምሮ ወደ ላይ በእሳት መካከል እንዳለ የጋለ ብረት፣ ከወገቡም በታች እሳት ይመስል እንደ ነበር አየሁ፤ ደማቅ ብርሃንም በዙሪያው ነበር።


በዝናብ ቀን በደመና ውስጥ እንደሚታየው ቀስተ ደመና በዙሪያው ያለው ጸዳል እንዲሁ ነበር። ይህም የእግዚአብሔር ክብር መልክ አምሳያ ነበረ። ባየሁትም ጊዜ በግንባሬ ተደፋሁ፤ የአንድ ተናጋሪን ድምፅ ሰማሁ።


ቍጣውን ማን ሊቋቋም ይችላል? ጽኑ ቍጣውንስ ማን ሊሸከም ይችላል? መዓቱ እንደ እሳት ፈስሷል፤ ዐለቶችም በፊቱ ተሰነጣጥቀዋል።


አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚባላ እሳት፣ ቀናተኛም አምላክ ነውና።


ሊገሥጽህ ድምፁን ከሰማይ እንድትሰማ አደረገ፤ በምድርም ላይ አስፈሪ እሳቱን አሳየህ፤ ከእሳቱም ውስጥ ቃሉን ሰማህ።


ይሁን እንጂ እንደሚባላ እሳት ከፊትህ ቀድሞ የሚሻገረው አምላክህ እግዚአብሔር መሆኑን ዛሬ ርግጠኛ ሁን፤ እነርሱን ያጠፋቸዋል፤ በፊትህም ድል ያደርጋቸዋል፤ አንተም እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት ታስወጣቸዋለህ፤ በፍጥነትም ትደመስሳቸዋለህ።


ሊዳሰስ ወደሚችለውና በእሳት ወደሚቃጠለው ተራራ፣ ወደ ጨለማው፣ ወደ ጭጋጉና ወደ ዐውሎ ነፋሱ አልደረሳችሁም፤


“አምላካችን የሚባላ እሳት ነውና።”


跟着我们:

广告


广告