Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 22:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “አንድ ሰው ከብቶቹን በመስክ ወይም በወይን ቦታ አሰማርቶ እንዲሁ ስድ ቢለቅቃቸውና የሌላውን ሰው መስክ ቢግጡ፣ ምርጥ ከሆነው ከራሱ መስክ ወይም የወይን ቦታ መክፈል አለበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እሳት ቢነሣ፥ እሾኽንም ቢይዝ፥ ክምሩንም ወይም ያልታጨደውን እህል ወይም እርሻውን ቢያቃጥል፥ እሳቱን ያነደደው ይካስ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “አንድ ሰው እንስሶቹ በመስክ ወይም በወይን ተክል ቦታ አሰማርቶ ሳለ እንስሶቹ ወደ ሌላ ሰው እርሻ ገብተው ሰብሉን ቢበሉት ከራሱ ማሳ ወይም የወይን ተክል ቦታ ከሚያገኘው ምርት ካሣ ይክፈል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 “የሰ​ውን አዝ​መራ ከብ​ቱን ያስ​በላ፥ የሌላ ሰው ወይ​ን​ንም ያስ​በላ ሰው ቢኖር ግም​ቱን ይክ​ፈል። የሰ​ውን አዝ​መራ ፈጽሞ ቢያ​ስ​በላ ግን በአ​ጠ​ገቡ ባለ አዝ​መራ ልክ ይክ​ፈል፤ ወይ​ንም ቢሆን በአ​ጠ​ገቡ ባለ ወይን ልክ ይክ​ፈል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ማንም ሰው ወደ እርሻ ወይም ወደ ወይን ስፍራ ከብቱን ቢነዳው፥ የሌላውንም እርሻ ቢያስበላ፥ ከተመረጠ እርሻው ከማለፊያውም ወይኑ ይካስ።

参见章节 复制




ዘፀአት 22:5
7 交叉引用  

የለፋበትን ሳይበላው ይመልሳል፤ ከንግዱም ባገኘው ትርፍ አይደሰትም፤


የጕድጓዱ ባለቤት ኪሳራ ይክፈል፤ ለባለቤቱ መክፈል አለበት፤ የሞተውም እንስሳ ለርሱ ይሆናል።


እንስሳው ከጎረቤት ተሰርቆ ከሆነ ግን፣ ለባለቤቱ ካሳ መክፈል አለበት።


ነገር ግን ፀሓይ ከወጣች በኋላ ከተፈጸመ፣ ሰውየው በነፍስ ግድያ ይጠየቃል። “ሌባ የሰረቀውን መክፈል አለበት፤ ምንም ከሌለው ግን የሰረቀውን ይከፍል ዘንድ ይሸጥ።


የሰረቀው እንስሳ በሬ ወይም አህያ ወይም በግ ከነሕይወቱ በእጁ ከተያዘ ዕጥፍ መክፈል አለበት።


“እሳት ተነሥቶ ወደ ቍጥቋጦ ቢዘምትና ክምርን ወይም ያልታጨደን እህል ወይም አዝመራውን እንዳለ ቢበላ፣ እሳቱን ያቀጣጠለው ሰው ካሳ ይክፈል።


ከዚህም በቀር አንተ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ምድር አላመጣኸንም፤ ወይም ዕርሻዎችንና የወይን ተክል ቦታዎች አላወረስኸንም። ታዲያ የእነዚህን ሰዎች ዐይን ታወጣለህን? በጭራሽ አንመጣም!”


跟着我们:

广告


广告