Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 22:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 “ለእግዚአብሔር በቀር ለሌላ አማልክት የሚሠዋ ይጥፋ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ስደተኛውን አትበድለው፥ አትጨቁነውም፥ እናንተም በግብጽ ምድር ስደተኞች ነበራችሁና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 “ለእግዚአብሔር ካልሆነ በቀር ለሌላ ለማንኛውም አምላክ መሥዋዕት የሚያቀርብ በሞት ይቀጣ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ በቀር ለአ​ማ​ል​ክት የሚ​ሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ከእግዚአብሔር በቀር ለአንዳች አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ።

参见章节 复制




ዘፀአት 22:20
20 交叉引用  

ከዚያም ኤልያስ፣ “የበኣልን ነቢያት ያዟቸው! አንድም ሰው እንዳያመልጥ” ሲል አዘዘ፤ ሕዝቡም ያዟቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ አውርዶ አሳረዳቸው።


ኢዩ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቅርቦ እንዳበቃ ጠባቂዎቹንና የጦር አለቆቹን፣ “ግቡና ግደሏቸው፤ ማንም እንዳያመልጥ” ሲል አዘዘ። እነርሱም በሰይፍ ፈጇቸው፤ ጠባቂዎቹና የጦር ሹማምቱም ሬሳውን በሙሉ ወደ ውጭ አውጥተው ጣሉ። ከዚያም ወደ ውስጠኛው የበኣል ቤተ ጣዖት ገቡ።


የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ ሁሉ ግን፣ ትንሽም ሆነ ትልቅ፣ ወንድም ሆነ ሴት እንዲገደል አደረጉ።


“መጻተኛውን አትጨቍን፤ በግብጽ መጻተኛ ስለ ነበራችሁ፣ መጻተኛ ምን እንደሚሰማው እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁና።


“ካዘዝኋቸው ፈቀቅ ለማለት ፈጣኖች ሆኑ፤ ለራሳቸውም በጥጃ ምስል የተቀረጸ ጣዖትን ሠሩ፤ ለርሱም ሰገዱለት፤ ሠዉለትም፤ እንዲሁም፣ ‘እስራኤል ሆይ፤ ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ እነዚህ ናቸው’ አሉ።”


“በምድሪቱ ከሚኖሩት ጋራ ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም አምላኮቻቸውን ተከትለው ባመነዘሩና መሥዋዕትም ባቀረቡላቸው ጊዜ ይጋብዙሃል፤ አንተም መሥዋዕታቸውን ትበላለህ።


እኔም፣ “እያንዳንዳችሁ ዐይኖቻችሁን ያሳረፋችሁባቸውን ርኩስ ምስሎች አስወግዱ፤ በግብጽ ጣዖታትም ራሳችሁን አታርክሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ” አልኋቸው።


ከዚህ በፊት ላመነዘሩባቸው አጋንንት ከእንግዲህ ወዲህ ማንኛውንም መሥዋዕት ሊሠዉ አይገባም። ይህ ለእነርሱና ከእነርሱ በኋላ ለሚነሣው ትውልድ ሁሉ የዘላለም ሥርዐት ይሁን።’


“ ‘መጻተኛ በምድራችሁ ላይ ዐብሯችሁ በሚኖርበት ጊዜ አትበድሉት፤


“ስለዚህ እኔ ለፍርድ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በመተተኞች፣ በአመንዝራዎች፣ በሐሰት በሚምሉ፣ የሠራተኞችን ደመወዝ በሚከለክሉ፣ መበለቶችንና ድኻ አደጉን በሚጨቍኑ፣ መጻተኞችን ፍትሕ በሚነፍጉ፣ እኔንም በማይፈሩት ላይ እመሰክርባቸው ዘንድ እፈጥናለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልመና ሰምቶ ከነዓናውያንን በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ሰዎቹንና ከተሞቻቸውን ፈጽመው ደመሰሱ፤ ከዚህ የተነሣም ስፍራው ሖርማ ተባለ።


እርሱ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች ይፈርዳል፤ መጻተኛውንም ምግብና ልብስ በመስጠት ይወድዳል።


ነገር ግን እንዲናገር እኔ ያላዘዝሁትን ቃል በድፍረት በስሜ የሚናገርም ሆነ በሌሎች አማልክት ስም የሚናገር ነቢይ ይገደል።”


ለእነርሱ የተወለዱላቸው የሦስተኛው ትውልድ ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ መግባት ይችላሉ።


ለመጻተኛው ወይም አባት ለሌለው ልጅ ፍትሕ አትንፈገው፤ የመበለቲቱንም መደረቢያ መያዣ አታድርግ።


跟着我们:

广告


广告