Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 21:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ለርሱ ትሆነው ዘንድ የመረጣትን ጌታዋን ደስ ባታሠኝ፣ በወጆ ይስደዳት፤ ለባዕዳን ይሸጣት ዘንድ መብት የለውም፤ ምክንያቱም ለርሷ ያለውን ታማኝነት አጓድሏልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጌታዋን ደስ ባታሰኘው እንድትዋጅ ይስጣት፤ በድሎአታልና ለባዕድ ሕዝብ ሊሸጣት መብት የለውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሚስት ሊያደርጋት ለፈለገ ሰው ብትሸጥና በኋላም እርሱ ሳይወዳት ቢቀር ተመልሳ በሕዝብዋ ትዋጅ ጌታዋ የማይገባ ነገር ስላደረገባት ለባዕድ ሊሸጣት አይችልም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ለእ​ርሱ ከታ​ጨች በኋላ ጌታ​ዋን ደስ ባታ​ሰ​ኘው በዎጆ ይስ​ደ​ዳት፤ ነገር ግን ለሌላ ወገን ይሸ​ጣት ዘንድ አይ​ገ​ባ​ውም። እርሱ አር​ክ​ሶ​አ​ታ​ልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ጌታዋን ደስ ባታሰኘው በዎጆ ይስደዳት፤ ስለ ናቃት ለሌላ ወገን ሰዎች ይሸጣት ዘንድ አይገባውም።

参见章节 复制




ዘፀአት 21:8
13 交叉引用  

በዚህም የከነዓናውያን ሴቶች በአባቱ በይሥሐቅ ዘንድ የቱን ያህል የተጠሉ መሆናቸውን ተገነዘበ፤


ወንድሞቼ ግን እንደማያዛልቅ ጅረት፣ ለጊዜው ሞልቶ እንደሚፈስስ ወንዝ የማይታመኑ ናቸው፤


“አንድ ሰው ሴት ልጁን አገልጋይ እንድትሆን ቢሸጣት፣ እንደ ወንዶቹ አገልጋዮች በነጻ መሸኘት የለባትም።


ለወንድ ልጁ ትሆን ዘንድ መርጧት ከሆነ እንደ ራሱ ልጅ የሚገባትን መብት ይስጣት።


ሙሴም እንዲህ አለ፤ “ከአንተ እንደ ተለየሁ ወዲያውኑ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ነገም ዝንቡ ሁሉ ከፈርዖን፣ ከሹማምቱና ከሕዝቡ ይወገዳል። ብቻ ሕዝቡ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዲሠዉ ባለመፍቀድ ከዚህ ቀደም ፈርዖን አታልሎ እንዳደረገው አሁንም እንዳያደርግ ርግጠኛ ይሁን።”


ታማኝነትን ከማጕደላቸው የተነሣ ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”


ሚስት አጭቶ ያላገባት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፤ አለዚያ በጦርነቱ ይሞትና ሌላ ሰው ያገባታል።”


አባቱና እናቱም፣ “ከዘመዶችህ ወይም ከሕዝባችን ሁሉ መካከል ለአንተ የምትሆን ሴት መች ታጣችና ነው ወዳልተገረዙት ፍልስጥኤማውያን ሚስት ፍለጋ የሄድኸው?” አሉት። ሳምሶንም አባቱን፣ “ልቤን የማረከችው እርሷ ናትና እርሷን አጋባኝ” አለው።


እንግዲህ ዛሬ በይሩባኣልና በቤተ ሰቡ ላይ ያደረጋችሁት በእውነትና ያለ እንከን ከሆነ እናንተ በአቢሜሌክ ደስ ይበላችሁ፤ እርሱም በእናንተ ደስ ይበለው!


ሳኦል እጅግ ተቈጣ፤ ይህም ነገር አላስደሰተውም። እርሱም፣ “ለዳዊት ዐሥር ሺሕ አሉለት፤ ለእኔ ግን ሺሕ ብቻ! እንግዲህ መንግሥት እንጂ ሌላ ምን ቀረው” አለ።


ነገር ግን፣ “የሚመራን ንጉሥ አንግሥልን” ማለታቸው ሳሙኤልን አላስደሰተውም፤ ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤


跟着我们:

广告


广告