Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 21:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 አንድ ሰው በተንኰል ሆነ ብሎ ሌላውን ቢገድል፣ ከመሠዊያዬ ተወስዶ ይገደል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሰው ግን ቢደፍር፥ ባልጀራውንም በተንኮል ቢገድለው፥ እንዲገደል ከመሠዊያዬ አውጥተህ ውሰደው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ይሁን እንጂ ሰው በቊጣ ተነሣሥቶና ሆን ብሎ ሌላ ሰው ቢገድል፥ ሕይወቱን ለማዳን ወደ መሠዊያዬ ሸሽቶ ቢሄድ በሞት ይቀጣ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሰው ግን ቢሸ​ምቅ ጠላ​ቱ​ንም በተ​ን​ኰል ቢገ​ድ​ለ​ውና ቢማ​ፀን፥ እን​ዲ​ገ​ደል ከመ​ሠ​ዊ​ያዬ አው​ጥ​ተህ ውሰ​ደው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሰው ግን ቢደፍር፥ ባልጀራውን በተንኮል ቢገድለው፥ እንዲሞት ከመሠዊያዬ አውጥተህ ውሰደው።

参见章节 复制




ዘፀአት 21:14
18 交叉引用  

አበኔር ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፣ ኢዮአብ በቈይታ የሚያነጋግረው በመምሰል ዞር አድርጎ ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሲል፣ ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው።


ካህኑ ዮዳሄም የወታደሮች አዛዥ ወደሆኑት የመቶ አለቆች፣ “በረድፍ በተሰለፉት ጭፍሮች መካከል አውጧት፤ የሚከተላትንም ሁሉ በሰይፍ ግደሉት” ሲል አዘዘ፤ ይህ የሆነውም ካህኑ አስቀድሞ፣ “በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገደል የለባትም” በማለቱ ነበር።


ባሪያህን ከድፍረት ኀጢአት ጠብቅ፤ እንዳይሠለጥንብኝም ርዳኝ፤ ያን ጊዜ ያለ እንከን እሆናለሁ፤ ከታላቅ በደልም እነጻለሁ።


“አባቱን ወይም እናቱን የሚመታ ይገደል።


የሰው ደም ያለበት ሰው፣ ዕድሜ ልኩን ሲቅበዘበዝ ይኖራል፤ ማንም ሰው አይርዳው።


“ ‘አንድ ሰው ሌላውን እንዲሞት በብረት ቢመታው ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በሞትም ይቀጣል።


እኔም ነገርኋችሁ፤ እናንተ ግን አላደመጣችሁም፤ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዐምፃችሁ፣ በትዕቢታችሁ ወደ ተራራማው አገር ዘመታችሁ።


ነቢዩ በእግዚአብሔር ስም የተናገረው ካልተፈጸመ ወይም እውነት ሆኖ ካልተገኘ፣ መልእክቱ እግዚአብሔር የተናገረው አይደለም። ያ ነቢይ በድፍረት ተናግሮታልና እርሱን አትፍራው።


“በድብቅ ባልንጀራውን የሚገድል የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።


የእውነትን ዕውቀት ከተቀበልን በኋላ ሆነ ብለን በኀጢአት ጸንተን ብንመላለስ፣ ከእንግዲህ ለኀጢአት የሚሆን ሌላ መሥዋዕት አይኖርም፤


በተለይም በርኩስ ምኞት የሥጋ ፍላጎታቸውን የሚከተሉትንና ሥልጣንን የሚንቁትን ለፍርድ ጠብቆ ያቈያቸዋል። እነዚህ ሰዎች ደፋሮችና እብሪተኞች ስለ ሆኑ ሰማያውያንን ፍጡራን ሲሳደቡ አይፈሩም፤


跟着我们:

广告


广告