Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 19:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡት ካህናት እንኳ ራሳቸውን መቀደስ አለባቸው፤ አለዚያ እግዚአብሔር ቍጣውን ያወርድባቸዋል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ወደ ጌታ የሚቀርቡት ካህናትም ራሳቸውን ይቀድሱ ካልሆነ ግን ጌታ ያጠፋቸዋል።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ለአገልግሎት ወደ እኔ የሚቀርቡ ካህናት እንኳ ሳይቀሩ ራሳቸውን ያንጹ፤ ይህ ካልሆነ እኔ እግዚአብሔር እቀጣቸዋለሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ቀ​ር​ቡት ካህ​ናት ደግሞ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ራሳ​ቸ​ውን ይቀ​ድሱ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ወደ እግዚአብሔርም የሚቀርቡት ካህናት ደግሞ እግዚአብሔር እንዳያጠፋቸው ራሳቸውን ይቀድሱ አለው።

参见章节 复制




ዘፀአት 19:22
17 交叉引用  

የአምላካችን የእግዚአብሔር ቍጣ በላያችን ላይ እንዲህ የነደደው እናንተ ሌዋውያኑ ቀድሞም ስላላመጣችሁት ነው፤ እኛም ብንሆን ምን ማድረግ እንዳለብን በታዘዘው መሠረት አልጠየቅነውም።”


በሁለተኛው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካውን በግ ዐረዱ። ካህናቱና ሌዋውያኑ ዐፍረው ስለ ነበር ራሳቸውን ቀደሱ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትንም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አመጡ።


በቂ ካህናት ራሳቸውን ስላልቀደሱና ሕዝቡም ገና በኢየሩሳሌም ስላልተሰበሰቡ፣ በዓሉን በወቅቱ ለማክበር አልቻሉም ነበር።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “ውረድና አሮንን ከአንተ ጋራ ይዘኸው ውጣ፤ ካህናቱና ሕዝቡ ግን ወደ እግዚአብሔር ለመምጣት መጣደፍ የለባቸውም፤ አለዚያ እርሱ ቍጣውን ያወርድባቸዋል።”


አሁንም በፍጹም ብትታዘዙኝና ቃል ኪዳኔን ብትጠብቁ እነሆ ከአሕዛብ ሁሉ እናንተ የተወደደ ርስቴ ትሆናላችሁ፤ ምንም እንኳ ምድር ሁሉ የእኔ ብትሆንም፣


ከዚያም ወጣት ወንድ እስራኤላውያንን ላከ፤ እነርሱም የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ ወይፈኖችን የኅብረት መሥዋዕት አድርገው ለእግዚአብሔር ሠዉ።


እናንተ የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ፣ ተለዩ! ተለዩ! ከመካከልዋ ውጡ፤ ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤ ከዚያ ውጡ ንጹሓንም ሁኑ፤


ለአምላካቸው የተቀደሱ ይሁኑ፤ የአምላካቸውንም ስም አያርክሱ። ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርበውን መሥዋዕት የአምላካቸውን ምግብ ስለሚያቀርቡ ቅዱሳን ይሁኑ።


“ለሕዝቡ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ነገ ሥጋ ትበላላችሁና ራሳችሁን በመቀደስ ተዘጋጁ። “በግብጽ ተመችቶን ነበር፤ አሁን ግን ሥጋ ማን ይሰጠናል!” ብላችሁ ያለቀሳችሁትን እግዚአብሔር ሰምቷል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ሥጋ ይሰጣችኋል፤ እናንተም ትበላላችሁ።


እርሷም ወዲያውኑ እግሩ ሥር ወድቃ ሞተች፤ ጕልማሶቹም ሲገቡ ሞታ አገኟት፤ አውጥተውም በባሏ አጠገብ ቀበሯት።


ሐናንያም ይህን እንደ ሰማ ወድቆ ሞተ፤ ይህን የሰሙትም ሁሉ ታላቅ ፍርሀት ያዛቸው።


跟着我们:

广告


广告