Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 19:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከራፊዲም ከተነሡ በኋላ ወደ ሲና ምድረ በዳ ገቡ፤ እስራኤልም በዚያ በምድረ በዳው በተራራው ፊት ለፊት ሰፈሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከራፊድም ተነሥተው ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ፥ በምድረ በዳም ሰፈሩ፤ በዚያም እስራኤል በተራራው ፊት ሰፈረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እነርሱም ከረፊዲም ተነሥተው ወደ ሲና በረሓ ተጒዘው በተራራው ፊት ለፊት ባለው በረሓ ሰፈሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ከራ​ፊ​ድም ተነ​ሥ​ተው ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ፤ በዚ​ያም እስ​ራ​ኤል በተ​ራ​ራው ፊት ሰፈሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ከራፊድም ተነሥተው ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ፥ በምድረ በዳም ሰፈሩ፤ በዚያም እስራኤል በተራራው ፊት ሰፈረ።

参见章节 复制




ዘፀአት 19:2
10 交叉引用  

መላው የእስራኤል ማኅበር ከሲና ምድረ በዳ ተነሥቶ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ከስፍራ ወደ ስፍራ ተጕዞ በራፊዲም ሰፈረ፤ ነገር ግን ሕዝቡ የሚጠጡት ውሃ አልነበረም።


አማሌቃውያን መጥተው እስራኤላውያንን ራፊዲም ላይ ወጉ፤


የሙሴ ዐማት ዮቶር ከሙሴ ወንድ ልጆችና ሚስት ጋራ ሆኖ በምድረ በዳ ከእግዚአብሔር ተራራ አጠገብ ወደ ሰፈረበት ወደ ሙሴ መጣ።


አንድ ቀን ሙሴ የምድያም ካህን የሆነውን የዐማቱን የዮቶር በጎችና ፍየሎች እየጠበቀ ሳለ፣ መንጋውን እየነዳ ወደ ምድረ በዳው ዳርቻ አምርቶ የእግዚአብሔር ተራራ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ኮሬብ ቀረበ።


እግዚአብሔርም፣ “እኔ ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤ እኔ የላክሁህ ለመሆኑ ምልክቱ ይህ ነው፤ ሕዝቡን ከግብጽ ካወጣሃቸው በኋላ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታመልካላችሁ” አለው።


እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን በሲና ምድረ በዳ ሳሉ እግዚአብሔር ሙሴን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ተናገረው፤ እንዲህም አለው፤


ከራፊዲም ተነሥተው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ።


“ከአርባ ዓመት በኋላ፣ በሲና ተራራ አካባቢ ባለው ምድረ በዳ፣ በቍጥቋጦው ውስጥ በሚንቀለቀል የእሳት ነበልባል መልአክ ተገለጠለት።


እርሱም በሲና ተራራ ከተናገረው መልአክና ከአባቶቻችን ጋራ በምድረ በዳ በሕዝቡ ጉባኤ መካከል ነበር፤ የሕይወትንም ቃል ወደ እኛ ለማስተላለፍ ተቀበለ።


እነዚህ ሴቶች ሁለቱን ኪዳኖች ስለሚያመለክቱ፣ ይህ ሁኔታ እንደ ምሳሌ የሚታይ ነው። አንደኛዋ ኪዳን ከሲና ተራራ ስትሆን፣ ለባርነት የሚሆኑ ልጆችን የምትወልድ ናት፤ እርሷም አጋር ናት።


跟着我们:

广告


广告