Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 18:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ሁልጊዜም የሕዝብ ዳኞች ሆነው አገለገሉ፤ አስቸጋሪ ጕዳዮችን ወደ ሙሴ አመጡ፤ ቀላል የሆነውን ራሳቸው ወሰኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በሕዝቡም ላይ ሁልጊዜ ፈረዱ፤ የከበዳቸውን ነገር ወደ ሙሴ አመጡ፥ ትንሹን ነገር ሁሉ ግን እነርሱ ፈረዱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እነርሱም ከባድ ያልሆኑ ጉዳዮችን በማየት ሕዝቡን ሁልጊዜ በዳኝነት ያገለግሉ ጀመር፤ አስቸጋሪ የሆኑትን ጉዳዮች ብቻ ወደ ሙሴ ሲያቀርቡ፥ ቀላል የሆነውን ጠብና ክርክር ሁሉ ራሳቸው ይወስኑ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በሕ​ዝ​ቡም ላይ ሁል​ጊዜ ፈረዱ፤ የከ​በ​ዳ​ቸ​ው​ንም ነገር ወደ ሙሴ አመጡ፤ ቀላ​ሉን ነገር ሁሉ ግን እነ​ርሱ ፈረዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በሕዝቡም ላይ ሁልጊዜ ፈረዱ፤ የከበደባቸውንም ነገር ወደ ሙሴ አመጡ፥ ታናሹን ነገር ሁሉ ግን እነርሱ ፈረዱ።

参见章节 复制




ዘፀአት 18:26
8 交叉引用  

የሳባ ንግሥት የሰሎሞንን ዝና እና ከእግዚአብሔር ስም ጋራ ያለውን ግንኙነት በሰማች ጊዜ፣ አስቸጋሪ በሆኑ ጥያቄዎች ልትፈትነው መጣች።


ለድኾች አባት፣ ለባይተዋሩ ተሟጋች ነበርሁ።


በማንኛውም ጊዜ ሕዝቡን ይዳኙ፤ ቀላሉን ነገር እነርሱ ይወስኑ፤ አስቸጋሪ የሆነውን ጕዳይ ሁሉ ግን ለአንተ እንዲያቀርቡ አድርግ፤ ሥራውን ስለሚያግዙህ ሸክምህ ይቃለላል።


የእስራኤላዊቱ ልጅ የእግዚአብሔርን ስም በማቃለል ሰደበ፤ ስለዚህም ወደ ሙሴ አመጡት፤ የሰውየው እናት ስም ሰሎሚት ነበር፤ እርሷም ከዳን ወገን የተወለደው የደብራይ ልጅ ነበረች።


በፍርድ አድልዎ አታድርጉ፤ ትልቁንም ትንሹንም እኩል እዩ፤ ፍርድ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ፣ ማንኛውንም ሰው አትፍሩ። ከዐቅማችሁ በላይ የሆነውን ሁሉ ወደ እኔ አምጡት፤ እኔ አየዋለሁ።”


በአንድ የነፍስ ግድያ ዐይነትና በሌላ፣ በአንድ ዐይነት ሕጋዊ ክርክርና በሌላ፣ ወይም በአንድ የክስ ዐይነትና በሌላ መካከል ውሳኔ የሚጠይቅ ማንኛውም ጕዳይ ቢነሣ፣ ከዐቅምህ በላይ የሆነ ጕዳይ በከተሞችህ ውስጥ ቢያጋጥምህ፣ ተነሥተህ አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ስፍራ ውጣ፤


跟着我们:

广告


广告