Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 18:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ሥርዐቶቹንና ሕጎቹን አስተምራቸው፤ እንዴት መኖር እንዳለባቸውና ምን መሥራት እንደሚገባቸው አሳያቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ሥርዓቱንና ሕጉን አስተምራቸው፥ የሚሄዱበትን መንገድና የሚያደርጉትን ሥራ አሳውቃቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 አንተ የእግዚአብሔርን ሥርዓትና ሕግ ልታስተምራቸው፥ እንዲሁም እንዴት መኖርና ምን ማድረግ እንደሚገባቸውም ልትገልጥላቸው ይገባል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥር​ዐ​ቱ​ንና ሕጉን መስ​ክ​ር​ላ​ቸው፤ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ት​ንም ሥራ ሁሉ አሳ​ያ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሥርዓቱንም ሕጉንም አስተምራቸው፥ የሚሄዱበትን መንገድ የሚያደርጉትንም ሥራ ሁሉ አሳያቸው።

参见章节 复制




ዘፀአት 18:20
21 交叉引用  

በአንተ ታምኛለሁና፣ በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና፣ የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ።


አስተምርሃለሁ፤ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ እመክርሃለሁ፤ በዐይኔም እከታተልሃለሁ።


ክርክር በኖራቸው ቍጥር ጕዳያቸው ወደ እኔ ይመጣል፤ ለግራና ለቀኙ የሚሆነውን እኔ ወስኜ የእግዚአብሔርን ሥርዐትና ሕጎች እነግራቸዋለሁ።”


ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዘወር ብትል ጆሮህ ከኋላህ፣ “መንገዱ ይህ ነው፤ በርሱ ሂድ” የሚል ድምፅ ይሰማል።


አምላክህ እግዚአብሔር ወዴት መሄድ እንዳለብንና ምን ማድረግ እንደሚገባን እንዲነግረን ጸልይልን።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “መንታ መንገድ ላይ ቁሙ፣ ተመልከቱም፤ መልካሟን፣ የጥንቷን መንገድ ጠይቁ፤ በርሷም ላይ ሂዱ። ለነፍሳችሁ ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እናንተ ግን፣ ‘በርሷ አንሄድም’ አላችሁ።


“የሰው ልጅ ሆይ፤ ለእስራኤል ቤት ጕበኛ አድርጌሃለሁ፤ ስለዚህ የምናገረውን ቃል ስማ፤ የምነግርህንም ማስጠንቀቂያ አስተላልፍላቸው።


ብዙ አሕዛብ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ በጐዳናውም እንድንሄድ፣ መንገዱን ያስተምረናል።” ሕግ ከጽዮን፤ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።


ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው፤ እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋራ ነኝ።”


ይህም ቤቱን ለባሮቹ ትቶ፣ እያንዳንዱን አገልጋይ በየሥራ ድርሻው ላይ አሰማርቶ፣ በረኛው ነቅቶ እንዲጠብቅ አዝዞ የሄደውን ሰው ይመስላል።


በዚያ ጊዜ ማድረግ የነበረባችሁን ሁሉ ነገርኋችሁ።


አሁንም እስራኤል ሆይ፤ በሕይወት እንድትኖሩ፣ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር እንድትገቡና እንድትወርሱ የማስተምራችሁን ሥርዐትና ሕግ ስሙ፤ ጠብቋቸውም።


ገብታችሁ በምትወርሷት ምድር፣ እንድትፈጽሟቸው እግዚአብሔር አምላኬ ባዘዘኝ መሠረት ሥርዐትንና ሕግን አስተምሬአችኋለሁ።


ሙሴ እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ እስራኤል ሆይ፤ በዛሬዋ ዕለት በጆሯችሁ የምነግራችሁን ሥርዐትና ሕግ ስሙ፤ አጥኗቸው፤ በጥንቃቄም ጠብቋቸው።


አንተ ቅረብ፤ አምላካችን እግዚአብሔር የሚለውን ሁሉ ስሙ፤ ከዚያም አምላካችን እግዚአብሔር የሚነግርህን ሁሉ ንገረን፤ እኛም እንሰማለን፤ እናደርገዋለንም።”


ስለዚህ በዛሬው ቀን የምሰጥህን ትእዛዙን፣ ሥርዐቱንና ሕግጋቱን ለመከተል ጥንቃቄ አድርግ።


በቀረውስ ወንድሞች ሆይ፤ እግዚአብሔርን ደስ ለማሠኘት እንዴት መኖር እንደሚገባችሁ አስተምረናችኋል፤ በርግጥም እንደዚያው እየኖራችሁ ነው። ስለ ሆነም በጌታ በኢየሱስ የምንለምናችሁና የምንመክራችሁ ከዚህ በበለጠ ሁኔታ በዚሁ እንድትገፉበት ነው።


ከዚህም በላይ እኔ ለእናንተ ከመጸለይ ወደ ኋላ በማለት እግዚአብሔርን መበደል ከእኔ ይራቅ፤ እኔ መልካምና ቅን የሆነውን መንገድ አስተምራችኋለሁ።


跟着我们:

广告


广告