Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 18:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ክርክር በኖራቸው ቍጥር ጕዳያቸው ወደ እኔ ይመጣል፤ ለግራና ለቀኙ የሚሆነውን እኔ ወስኜ የእግዚአብሔርን ሥርዐትና ሕጎች እነግራቸዋለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ነገርም ቢኖራቸው ወደ እኔ ይመጣሉ፥ በአንድ ሰውና በጎረቤቱ መካከል እፈርዳለሁ፥ የእግዚአብሔርንም ሥርዓትና ሕግ አስታውቃቸዋለሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሁለት ሰዎች ተጣልተውም ወደ እኔ ቢመጡ የትኛው ወገን ትክክል እንደሆን ለማሳወቅ የእግዚአብሔርን ሕግና ሥርዓት እነግራቸዋለሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ነገ​ርም ቢኖ​ራ​ቸው ወደ እኔ ይመ​ጣሉ፤ በዚ​ህና በዚያ ሰውም መካ​ከል እፈ​ር​ዳ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥር​ዐ​ትና ሕግ አስ​ታ​ው​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ነገርም ቢኖራቸው ወደ እኔ ይመጣሉ፥ በዚህና በዚያ ሰውም መካከል እፈርዳለሁ፥ የእግዚአብሔርንም ሥርዓትና ሕግ አስታውቃቸዋለሁ አለው።

参见章节 复制




ዘፀአት 18:16
20 交叉引用  

ከዚያም አቤሴሎም፣ “ተመልከት! ጕዳይህማ ትክክልና ተገቢም ነው፤ የትኛው የንጉሥ እንደራሴ ነው ታዲያ የሚያይልህ?” ይለዋል።


በየከተማው ከሚኖሩት ወገኖቻችሁ ስለ ደም መፋሰስ ወይም ሕግን፣ ትእዛዞችን፣ ደንብንና ሥርዐትን ስለ መተላለፍ በሚቀርብላችሁ በማናቸውም ጕዳይ እግዚአብሔርን እንዳይበድሉ አስጠንቅቋቸው፤ አለዚያ ግን ቍጣው በእናንተና በወንድሞቻችሁ ላይ ይመጣል፤ ይህን ብታደርጉ በደለኞች አትሆኑም።


“ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቼ አቤቱታ ባቀረቡ ጊዜ፣ ፍርድ አዛብቼ ከሆነ፣


የሙሴ ዐማት መልሶ እንዲህ አለው። “የምትሠራው መልካም አይደለም።


በማግስቱም በወጣ ጊዜ ሁለት ዕብራውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አየ፤ ጥፋተኛውንም፣ “የገዛ ወገንህን የምትመታው ለምንድን ነው?” አለው።


ከሐሰት ክስ ራቅ፤ በደል የሌለበትን ወይም ጻድቁን ሰው ለሞት አሳልፈህ አትስጥ፣ በደለኛውን ንጹሕ አላደርግምና።


እርሱም ሽማግሌዎችን “ወደ እናንተ እስክንመለስ ድረስ በዚህ ቈዩ፤ አሮንና ሖር ከእናንተ ጋራ ናቸው፤ ክርክር ያለው ባለጕዳይ ቢኖር ወደ እነርሱ ይሂድ።” አላቸው።


እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘ማንም ሰው አምላኩን ቢሳደብ ኀጢአት ሠርቷልና ይጠየቅበታል።


ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “ሰውየው ይሙት፤ መላውም ማኅበር ከሰፈር ውጭ በድንጋይ ይውገረው” አለው፤


ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው፤ እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋራ ነኝ።”


ከመካከላችሁ አንድ ሰው ከሌላው ጋራ ሙግት ቢኖረው፣ ጕዳዩን በቅዱሳን ፊት በማቅረብ ፈንታ እንዴት ደፍሮ በዐመፀኞች ፊት ለመፋረድ ያቀርባል?


ገብታችሁ በምትወርሷት ምድር፣ እንድትፈጽሟቸው እግዚአብሔር አምላኬ ባዘዘኝ መሠረት ሥርዐትንና ሕግን አስተምሬአችኋለሁ።


ሙሴ እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ እስራኤል ሆይ፤ በዛሬዋ ዕለት በጆሯችሁ የምነግራችሁን ሥርዐትና ሕግ ስሙ፤ አጥኗቸው፤ በጥንቃቄም ጠብቋቸው።


ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር እንድትጠብቁት አስተምራችሁ ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሰጠኝ ትእዛዝ፣ ሥርዐትና ሕግ ይህ ነው፤


ከዚህም በላይ እኔ ለእናንተ ከመጸለይ ወደ ኋላ በማለት እግዚአብሔርን መበደል ከእኔ ይራቅ፤ እኔ መልካምና ቅን የሆነውን መንገድ አስተምራችኋለሁ።


跟着我们:

广告


广告