Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 16:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እርሱም አላቸው፤ “እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፤ ‘ነገ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሰንበት በመሆን፣ የዕረፍት ቀን ይሆናል።’ ስለዚህ መጋገር የምትፈልጉትን ጋግሩ፤ መቀቀል የምትፈልጉትን ቀቅሉ። የተረፈውን አስቀምጡ፤ እስከ ጧትም ድረስ አቈዩት።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ የተናገረው ይህ ነው፦ ነገ የዕረፍት ሰንበት ነው፥ ለጌታ የተቀደሰ ሰንበት ነው፤ የምትጋግሩትን ጋግሩ፥ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፥ የተረፈውን ሁሉ ተውት ለጥዋት ለእናንተ አስቀምጡት።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “የነገው ዕለት ለእርሱ ተለይቶ የተቀደሰ የዕረፍት ቀን እንዲሆን እግዚአብሔር አዞአል፤ ስለዚህ ዛሬውኑ የምትጋግሩትን ጋግሩ፤ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፤ የተረፈው ተከፍሎ ለነገ ይቀመጥ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ሙሴም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረው ይህ ነው፦ ነገ ዕረ​ፍት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቀ​ደሰ ሰን​በት ነው፤ ነገ የም​ት​ጋ​ግ​ሩ​ትን ዛሬ ጋግሩ፤ የም​ት​ቀ​ቅ​ሉ​ት​ንም ቀቅሉ፤ የተ​ረ​ፈ​ው​ንም ሁሉ ለነገ እን​ዲ​ጠ​በቅ አኑሩ” አላ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እርሱም፦ እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው፦ ነገ ዕረፍት፥ ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ሰንበት ነው፤ የምትጋግሩትን ጋግሩ፥ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፥ የተረፈውን ሁሉ ለነገ እንዲጠበቅ አኑሩት አላቸው።

参见章节 复制




ዘፀአት 16:23
16 交叉引用  

“በሲና ተራራ ላይ ወረድህ፤ ከሰማይም ተናገርሃቸው። ትክክለኛ ደንቦችንና እውነተኛ ሕጎችን፣ መልካም ሥርዐቶችንና ትእዛዞችን ሰጠሃቸው።


የተቀደሰች ሰንበትህን አስታወቅሃቸው፤ ትእዛዞችን፣ ሥርዐቶችንና ሕጎችን በባሪያህ በሙሴ አማካይነት ሰጠሃቸው።


ሙሴም፣ “ማንም ከዚህ ለነገ ምንም ማስተረፍ የለበትም” አላቸው።


“ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ በሬህና አህያህ በቤትህ የተወለደው ባሪያና መጻተኛው ያርፉ ዘንድ በሰባተኛው ቀን ምንም አትሥራ።


ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ በሰንበት ቀን ማንም ቢሠራ በሞት መቀጣት አለበት።


አባቶቻችሁን እንዳዘዝኋቸው ሰንበትን አክብሩ እንጂ በሰንበት ቀን ከየቤታችሁ ሸክም ይዛችሁ አትውጡ፤ ምንም ሥራ አትሥሩ።”


“ ‘ሥራ የምትሠሩበት ስድስት ቀን አላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት፣ የተቀደሰ ጉባኤ ዕለት ነው። የእግዚአብሔር ሰንበት ስለ ሆነ፣ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ምንም ዐይነት ሥራ አትሥሩበት።


መናው እንደ ድንብላል ዘር ትንንሽ ሆኖ የሙጫ መልክ ነበረው።


ሕዝቡ ተዘዋውሮ በመልቀም በወፍጮ ከፈጨ ወይም በሙቀጫ ከወቀጠ በኋላ በምንቸት ይቀቅለው ወይም ይጋግረው ነበር፤ ጣዕሙም በወይራ ዘይት የተጋገረ ያህል ይጣፍጥ ነበር።


ከዚያም ተመልሰው ሽቱና ቅባት አዘጋጁ፤ ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት በሰንበት ቀን ዐረፉ።


አምላክህ እግዚአብሔር ባዘዘህ መሠረት የሰንበትን ቀን ቅዱስ አድርገህ አክብረው።


በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤ የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ከበስተ ኋላዬ ሰማሁ፤


跟着我们:

广告


广告