Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 15:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ቀላያትንም ለበሱ፤ እንደ ድንጋይ ወደ ጥልቁ ወረዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ቀላያትም ከደኑአቸው፤ እንደ ድንጋይ ወደ ባሕር ጥልቀት ወረዱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ጥልቁ ባሕር አሰጠማቸው፤ እንደ ድንጋይም አቈልቊለው ወደ ባሕሩ ጥልቀት ወረዱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ማዕ​በ​ልም ከደ​ና​ቸው፤ ወደ ባሕር ጥል​ቀት እንደ ድን​ጋይ ሰጠሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ቀላያትም ከደኑአቸው፤ ወደ ባሕር ጥልቀት እንደ ድንጋይ ሰጠሙ።

参见章节 复制




ዘፀአት 15:5
12 交叉引用  

በደረቅ ምድር እንዲሻገሩ ባሕሩን በፊታቸው ከፈልህ፤ ያሳደዷቸውን ግን በኀይለኛ ውሃ ውስጥ እንደሚጣል ድንጋይ ወደ ጥልቁ ውስጥ ወረወርሃቸው።


ባላንጦቻቸውን ውሃ ዋጣቸው፤ ከእነርሱም አንድ አልተረፈም።


ውሃውም ተመልሶ እስራኤላውያንን ተከትለው ወደ ባሕሩ የገቡትን ሠረገሎች፣ ፈረሰኞች፣ መላውን የፈርዖን ሰራዊት ሁሉ ሸፈነ። አንድም እንኳ አልተረፈም።


አንተ ግን እስትንፋስህን አነፈስህ፤ ባሕርም ከደናቸው፤ በኀያላን ውሆች፣ እንደ ብረት ሰጠሙ።


አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህ እስከሚያልፉ ድረስ፣ የተቤዠሃቸው ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፣ ድንጋጤና ሽብር በእነርሱ ላይ ይመጣል፤ በክንድህ ብርታት፣ እንደ ድንጋይ የማይንቀሳቀሱ ይሆናሉ።


ከውቅያኖሶች በፊት፣ የውሃ ምንጮች ከመፍለቃቸው በፊት ተወለድሁ፤


አሁን ግን በጥልቅ ውሃ ውስጥ፣ በባሕር ተንኰታኵተሻል፤ ጭነትሽና ተሳፋሪዎችሽ ሁሉ፣ ከአንቺ ጋራ ሰጥመዋል።


እንዲህም አለ፤ “ተጨንቄ ሳለሁ ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ፤ እርሱም መለሰልኝ፤ ከመቃብሩም ጥልቅ ርዳታን ፈልጌ ተጣራሁ፤ አንተም ጩኸቴን ሰማህ።


ተመልሰህ ትራራልናለህ፤ ኀጢአታችንን በእግርህ ትረግጣለህ፤ በደላችንንም ሁሉ ወደ ጥልቁ ባሕር ትጥላለህ።


“ነገር ግን ማንም በእኔ ከሚያምኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ከሚያሰናክል፣ ከባድ የወፍጮ ድንጋይ በዐንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር ተጥሎ ቢሰጥም ይሻለዋል።


ከዚያም አንድ ብርቱ መልአክ፣ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ የሚመስል ድንጋይ አንሥቶ ወደ ባሕር ወረወረው፤ እንዲህም አለ፤ “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን፣ እንዲህ ባለ ኀይል ትወረወራለች፤ ተመልሳም አትገኝም።


跟着我们:

广告


广告