ዘፀአት 10:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ምድሩ ሁሉ ጠቍሮ እስኪጨልም ድረስ አለበሱት። ከበረዶ የተረፈውን፣ በመስክ ላይ የበቀለውንና በዛፍ ላይ ያለውን ፍሬ ሁሉ ጠርገው በሉ። በግብጽ ምድር ሁሉ በዛፍ ላይ ወይም በተክል ላይ አንዳች ቅጠል አልተረፈም ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 የምድሩንም ፊት ሸፈኑት ምድሪቱም ጨለመች፤ የአገሪቱን ቡቃያ ሁሉ በረዶውም የተወውን በዛፉ የነበረውን ፍሬ ሁሉ በሉ፤ ለምለም ነገር በዛፉ ላይም በቡቃያው ላይም በግብጽ ምድር ሁሉ አልቀረም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 አገሪቱ ጠቊራ ጨለማ እስክትመስል ድረስ የአንበጣ መንጋ ሸፈናት፤ አንድም ነገር ሳያስቀር ከበረዶ የተረፈውን በየዛፉ ላይ የሚገኘውን ፍሬና ሌላውንም ተክል ሁሉ ግጦ በላው፤ በግብጽ ምድር ከሚገኘው ከማንኛውም ዛፍና ተክል ለምለም የሆነውን ቅጠል ሁሉ መድምዶ በላ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 የምድሩንም ፊት ፈጽሞ ሸፈነው፤ ሀገሪቱም ጠፋች፤ የሀገሪቱን ቡቃያ ሁሉ ከበረዶውም የተረፈውን፥ በዛፉ የነበረውን ፍሬ ሁሉ በላ፤ ለምለም ነገር በዛፎች ላይ፥ በእርሻውም ቡቃያ ሁሉ ላይ በግብፅ ሀገር ሁሉ አልቀረም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 የምድሩንም ፊት ፈጽመው ሸፈኑት፤ አገሪቱም ጨለመች፤ የአገሪቱን ቡቃያ ሁሉ በረዶውም የተወውን በዛፉ የነበረውን ፍሬ ሁሉ በሉ፤ ለምለም ነገር ዛፍም የምድር ሣርም በግብፅ አገር ሁሉ አልቀረም። 参见章节 |