አስቴር 9:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 በዚህ ጊዜ በሌሎች በንጉሡ አውራጃዎች የሚኖሩ የተቀሩት አይሁድ ራሳቸውን ለመከላከልና ከጠላቶቻቸውም ለመገላገል ተሰበሰቡ፤ ከሚጠሏቸውም ሰባ ዐምስት ሺሕ ገደሉ፤ በምርኮው ላይ ግን እጃቸውን አልዘረጉም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 እንዲሁም በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት በየሀገሩ የሚኖሩ አይሁድ ሁሉ አንድነታቸውን በማጠናከር ተደራጅተው ራሳቸውን ተከላከሉ፤ ይጠሉአቸው የነበሩትንም ሰባ አምስት ሺህ ሕዝብ በመግደል ከጠላቶቻቸው እጅ ራሳቸውን አዳኑ፤ ይሁን እንጂ ምንም ዐይነት የንብረት ዝርፊያ አላካሄዱም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 የቀሩትም በንጉሡ አገር ያሉ አይሁድ ተሰብስበው ለሕይወታቸው ቆሙ፥ ከጠላቶቻቸውም ዐረፉ፥ ከሚጠሉአቸውም ሰባ አምስት ሺህ ገደሉ፥ ነገር ግን ወደ ብዝበዛው እጃቸውን አልዘረጉም። 参见章节 |